የደቡብ አፍሪቃ ተማሪዎች ተቃውሞ | አፍሪቃ | DW | 16.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደቡብ አፍሪቃ ተማሪዎች ተቃውሞ

የደቡብ አፍሪቃ የዘር ግንኙነትን የሚያጠና ተቋም በህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል የጥቁሮች ቁጥር 16% ብቻ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ የሚበቁት ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆናቸውንም ተቋሙ በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው ጥናት ያትታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43

የደቡብ አፍሪቃ ተማሪዎች ተቃውሞ

የደቡብ አፍሪቃው ዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍያን በ10.5 በመቶ እንደሚጨምር ያስታወቀው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር። ውሳኔውን ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተከተሉት። ይህ ግን በተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ተማሪዎች ክፍያ መቀነስ አለበት (FeesMustFall) የሚል መፈክር አንግበው ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ። በተቃውሞው የመማሪያ ክፍሎች ተዘጉ፤ ፈተናዎች ተሰረዙ ተማሪዎችም ከፖሊስ ጋር ተጋጩ። የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ግን በትምህርት ላይ የተደረገውን ጭማሪ በመቃወም ብቻ አልተገታም። በትምህርት አገልግሎት ውስጥ ይስተዋላሉ ያሏቸውን የዘር እና ኤኮኖሚያዊ እኩልነት ጥያቄዎች አንስቷል። የደቡብ አፍሪቃ ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ኢ-እኩልነት በአፓርታይድ ዘመን ከነበረው የከፋ ነው ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ። የደቡብ አፍሪቃ የዘር ግንኙነትን የሚያጠና ተቋም (South African Institute of Race Relations) በህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል የጥቁሮች ቁጥር 16% ብቻ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ የሚበቁት ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆናቸውንም ተቋሙ በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው ጥናት ያትታል። ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ያነጋገርኩት የዶይቼ ቬለ የደቡብ አፍሪቃ ዘጋቢ መላኩ አየለ አንድ ተማሪ የሦስት አመት የዲግሪ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ እስከ 350,000 ራንድ መክፈል እንደሚጠበቅበት ጠቁሞኛል።

መላኩ አየለ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic