የደቡብ ሱዳን ግጭት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን | አፍሪቃ | DW | 30.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ግጭት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን

ንብረታቸውን ተዘርፈው ባዶ እጃቸውን ነው ወደ ጁባ የመጡት ። እኚሁ ነዋሪ ዝርፊያው በአማፅያኑም በመንግሥት ወታደሮችም እንደተካሄደ ነው የሚናገሩት ።

የደቡብ ሱዳኑ ግጭት መዘዝ እዚያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ተርፎ ዜጎች ለልዩ ልዩ ጥቃቶች መጋለጣቸውን መናገር ከጀመሩ ቆይተዋል ። በአሁኑ ጊዜ እዚያ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን የተወሰኑት በአውሮፕላንና በጀልባ ወደ ሃገራቸው እየተመለሱ ነው ። በስልክ ያነጋገርናቸው አንድ የጁባ ነዋሪ እንዳሉት በተለይ ግጭቱ ያየለባቸው አካባቢዎች የነበሩት ኢትዮጵያውን ሃብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ባዶ እጃቸውን ነው ወደ ጁባ የመጡት ። እኚሁ ነዋሪ ዝርፊያው በአማፅያኑም በመንግሥት ወታደሮችም እንደተካሄደ ነው የሚናገሩት ። በአሁኑ ሰዓት በደቡብ ሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በመደረግ ላይ ያለውንም ገልፀውልናል ።

በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን የሚደርስባቸው ስቃይ ሳያበቃ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በየተከሰተው የደቡብ ሱዳን ግጭት ሰላባ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ለመታገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ምን እያደረገ እንደሆነ ተክሌ የኋላ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አነጋግሯል።

ግጭት ከተቀሰቀሰበት ከታህሳስ 6 ቀን 2006ዓ,ም ጀምሮም 180 ሺህ የሚሆን ሕዝብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀሉን የተመድ አመልክቷል። ዛሬ አማፅያኑ ቦር ከተማን ለመያዝ እየገሰገሱ መሆናቸዉን ሲያመለክቱ የመንግስትኃይሎችም ከባድ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ እያስጠነቀቁ ነዉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ኗሪዎችም ሽሽት መጀመራቸዉ ተገልጿል።

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic