የደቡብ ሱዳን ይዞታና ኢትዮጵያዉያን | አፍሪቃ | DW | 26.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ይዞታና ኢትዮጵያዉያን

የለጋዋን ሀገር ደቡብ ሱዳንን ወቅታዊ የግጭት ጦርነት ሁኔታ ለማርገብና ተፋላሚዎቹ የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ነፃ አዉጭ ቡድን አመራሪዎች ለማስማማት ጥረቱ ቀጥሏል። እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ለስጋትና ዘረፋ ተጋልጠዋል።

ከዛሬ ቀደምም የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረትና የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት ድርጅት IGAD የዓመቱ ሊቀመንበር የሆኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደጁባ ፍጥጫዉን የሚያረግብ የልዑካን ቡድን ልከዋል። በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራዉ የልዑካን ቡድን ስላከናወኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ያነጋገረዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

በSMS የደረሱንን የስልክ ቁጥሮች በመጠቀም ወደደቡብ ሱዳን ለመደወል ብንሞክርም የብዙዎቹ ስልክ አልሰራልንም። ጁባኗሪ እንደሆኑ የገለፁልን አንድኢትዮጵያዊ ግን በተለያዩ የሀገሪቱ ግዛቶች በተለይም ኢትዮጵያዉያን በየሚኖሩበት የደረሰባቸዉን ችግር አስረድተዉናል። እሳቸዉ እንደሚሉት በተለይ መለካል በተባችዉ ግዛት የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ኢትዮጵያዉያኑን ጨምሮ ተዘርፈዋል፤ ዘራፊዎቹም የመንግስት የአማፂ ተብለዉ የሚለዩ አይደሉም፤ ሁሉም ካጋጠመዉ ዘራፊ እንደሆነ ነዉ ያመለከቱት። ቦር ከምትባለዉ ከተማ አማፅያኑ በመንግስት ኃይሎች ግፊት ወጥተዋል ቢባልም አካባቢዉን አሁን የተቆጣጠሩትም ከዝርፊያ እንዳልታቀቡ በስፍራዉ ከሚገኙ ወገኖች እንደተረዱም ገልጸዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic