1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የደቡብ ሱዳን የሰላም ተስፋ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2011

በደቡብ ሱዳን የሦስት ቀናት ጉብኝት ያደረገው የአፍሪቃ ኅብረት እና የተባበሩት መንሥታት ድርጅት የልዑካን ቡድን በሀገሪቱ ተስፋ ሰጪ የሆነ ሙሉ በሙሉ ግጭት የማቆም ርምጃ ማስተዋሉን ይፋ አደረገ። የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሞከሩትንም ተጠያቂ እንደሚያደርግም ቃል ገባ።

https://p.dw.com/p/36NEh
Äthiopien AU | PK über Süd Sudan Frieden Lage
ምስል DW/G. Tedla

ግጭት መቆሙ ለሰላም መስፈን ተስፋ ሰጪ ሆኗል

 ቡድኑ ባለፈው ወር መባቻ አዲስ አበባ ላይ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በደቡብ ሱዳን ለተጀመረው ሰላምን የማስፈን ጠንካራ ሥራ መሠረት መሆኑንም አመልክቷል። ጉብኝቱን አጠናቅቆ የተመለሰው የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽነር፤ የተመድ የሰላም አስከባሪ ስምሪት ኃላፊ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የሴቶች የድርጅት ተጠሪዎች የተካተቱበት ቡድን አዲስ አበባ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሎ ተከታዩን ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ