የደቡብ ሱዳን አቤቱታ | አፍሪቃ | DW | 15.02.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን አቤቱታ

ደቡብና ሰሜን ሱዳን አንዳቸዉ ሌላቸዉን ላይተነኩሱ በተፈራረሙ ማግስት ጥቃት ደረሰብኝ ስትል ጁባ አቤት ብላለች። ካርቱም ክሱን መሠረተ ቢስ እያለች ነዉ። እንዲያም ሆኖ ደቡብ ሱዳን በሰሜን ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የአየር ድብደባ ተፈፆሞብኛል ስትል፤

ለአፍሪቃዉ ኅብረት በፅሁፍ አቤቱታዋን አቅርባለች። በአፍሪቃ ኅብረትና በክፍለ ዓለሙ ሽማግሌዎች አማካኝነት ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ዳግም ላይጋጩ የተስማሙበት ዉል ከተፈረመ ሳምንት አልሞላዉም። አሁንም የአፍሪቃዉ ኅብረት የሁለቱ ወገኖች እሰጥ አገባ በዝግ ጉባኤ መመልከቱ ተገልጿል። ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የአቤቱታ አቅራቢዋን የደቡብ ሱዳንን ተወካይ ፓጋን አሙምን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አድርሶናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች