የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች እና የሰላሙ ድርድር | አፍሪቃ | DW | 04.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች እና የሰላሙ ድርድር

ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር በሚመሩት የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና በአንፃሩ በሚዋጋው የሪየክ ማቸር ያማፅያን ቡድን መካከል የሰላሙ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ እንደገና ጀመሩ ተሰምቷል። በዚሁ እአአ እስከ 12.08.2014 ዓም ድረስ በሚዘልቀው

ድርድር ከተፋላሚዎቹ ቡድኖች ሌላ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፣ የሲቭል ማህበረሰብ፣ የአፍሪቃ ህብረት፣ የተመድ ተወካዮች ተሳታፊዎች ሆነዋል። የሰላሙን ድርድር በሸምጋይነት የሚመራው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን፣ በምሕፃሩ «ኢጋድ» ተደራዳሪዎቹ በረሀብ አፋፍ ላይ የምትገኘዋን ሀገራቸውን ከዚሁ አደጋ ለመጠበቅ ባፋጣኝ ገላጋይ ሀሳብ እንዲደርሱ አሳስበዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ባለፈው ታህሳስ ወር በመዲናይቱ ጁባ ውጊያ ከተጀመረ ወዲህ ቢያንስ 10,000 ሰዎች ሲገደሉ ፣ እጅግ ብዙዎች ተፈናቅለዋል። ዛሬ ስለተጀመረዉ የሁለቱ ወገኖች የሰላም ድርድር ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic