የደቡብ ሱዳን ቀዉስና ሰባቱ ፖለቲከኞች | አፍሪቃ | DW | 14.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ቀዉስና ሰባቱ ፖለቲከኞች

የሰባቱ ፖለቲከኞች ቃል አቀባይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሬዝዳት ሳል ቫኪርን ሐገሪቱን ለዉጪ ሐይሎች አሳልፈዉ ስጥተዋል፤ ከጦርነትም ዶለዋታል በማለት ወቅሰዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የሳል ቫኪር መንግሥትን ከሥልጣን ለማስወገድ አሲራችኋል በሚል ወንጀል ከታሠሩ የሐገሪቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል በድርድር የተፈቱት ሰባቱ አዲስ አበባ በተያዘዉ ድርድር ላይ ለመካፈል እዚያዉ አዲስ አበባ ናቸዉ። ሰባቱ ፖለቲከኞች እነሱም ሆኑ አሁንም እስር ቤት የሚገኙት አራት ባልደረቦቻቸዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርገዋል የሚለዉን የመንግሥት ዉንጀላ አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል።የሰባቱ ፖለቲከኞች ቃል አቀባይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሬዝዳት ሳል ቫኪርን ሐገሪቱን ለዉጪ ሐይሎች አሳልፈዉ ስጥተዋል፤ ከጦርነትም ዶለዋታል በማለት ወቅሰዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሎት ነበር

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ


Audios and videos on the topic