የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 17.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ «ዩ ኤን ኤች ሲ አር» ባለፈው ዓርብ ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መካከል 16,000 ቹን አሁን ካሉበት አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር ጀምሮዋል።

ለወራት በዘለቀው የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት የተነሳ በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል። ከነዚህ መሸሻ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን « ኤን ኤች አር» በአሁኑ ሰዓት በድንበሩ አካባቢ የሚገኙ ወደ 16 000 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር ስራ በማካሄድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው « ኤን ኤች አር» የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔርን ለጊዜው የወከሉት / ቤተል ጌታቸው ስደተኞቹን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈሩ ሂደት ምን እንደሚመስል ገልፀውልናል።

ባለፈው ታህሳስ ወር በተቀሰቀሰው ግጭት የታወከችው ደቡብ ሱዳን እስካሁን አልተረጋጋችም። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ በግልፅ ለመናገር ቢከብድም፤ እንደ ኤን ኤች አር» ግምት ቶሎ አይሆንም። ወደሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ « ኤን ኤች አር» ከለላ ባገኙበት ቦታ ርዳታ ያቀርባል። ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 140 የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከለላ እንዳገኙ ድርጅቱ አክሎ አስረድቶዋል።

« ኤን ኤች አር» ዘገባ መሰረት በየቀኑ በአማካይ 20 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። በአምስት አቅጣጫዎች የሚገኘቱን ድንበሮቿን ለስደተኞች ክፍት ባደረገችው ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ጎርጎሮሲያኑ የካቲት 2014 መጨረሻ ብቻ በጠቅላላ 13 ሀገራት የሄዱ 500 143 የሚበልጡ ስደተኞች መመዝገባቸውን / ቤተል አስረድተዋል።

እነዚሁ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከየት ወዴት ነው የሚሰፍሩት? በምን ሁኔታስ ላይ ይገኛሉ? ለሁሉም መልስ ከድምፅ ዘገባው ያገኛሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic