የደቡብ ሱዳን ስምምነትና ገቢራዊነቱ | አፍሪቃ | DW | 25.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ስምምነትና ገቢራዊነቱ

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ በፕሬዚደንት ሳልቫኪር የሚመራው የጁባው መንግስት እና የቀድሞው የኣገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቻር የሚመሩት ኣማጺ ቡድን ተወካዮች ትናንት ማታ የተኩስ ኣቁም ስምምነት ተፈራርመዋል። አዲስ አበባ ዉስጥ የተፈረመዉ ሥምምነት ገቢራዊ የሚሆንበት መንገድ ግን እንዳጠያየቀ ነዉ።

በማሳቹሲትስ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዩንቨርስቲ የሁለቱ ሱዳኖች አጥኝ ፕሮፊሰር ኤሪክ ሬቨስ ስምምነቱ የደቡብ ሱዳን ደም አፋሳሽ ብጥብጥ ለማስወገድ በቂ አይደለም ባይ ናቸዉ።
አዲስ አበባ ላይ፤ በተፈረመዉ ስምምነት መሰረት አንድ ወር የዘለቀዉ ጦርነት በ24 ሰዓት ዉስጥ ማብቃት አለበት። በተጨማሪም በስምምነቱ መሰረት የደቡብ ሱዳን መንግስት፤ በጦርነቱ የያዛቸዉን፤ አስራ አንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በነጻ መልቀቅ ይኖርበታል። ግን ይህ ትናንት ማምሻዉን በሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች መካከል በፊርማ የፀደቀዉ የተኩስ አቁም ዉል ከወረቀት ባለፍ ፤ተግባራዊ ሆኖ ጦርነቱ ያበቃ ይሆን? ማሳቹሲትስ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዩንቨርስቲ የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ጉዳዮችን አዋቂ የሆኑት ፕሮፊሰር ኤሪክ ሬቨስ ሰላም እንዲመጣ እመኛለሁ ሲሉ ይመልሳሉ፤
« አዎ ሰላም እንዲመጣ እመኛለሁ ግን፤ ይህ ይከሰታል የሚል እምነት የለኝም። በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ብዙ ያለመግባባቶች ያለበት እና የተዛበ ጉዳይ፤ ከዝያም አልፎ ብዙ ትክክለኛ ያልሆኑ ጉዳዮች ተወርተዋል ተዘግበዋል። በእኔ ሃሳብ፤ ሪክ ማቸር፤ የሳልቫኪር ተቀናቃኝ ናቸዉ፤ በአሁኑ ወቅት አማጽያኑንም የሚመሩት እሳቸዉ ናቸዉ ተብሎ የሚታሰበዉ ነገር ፤ ከእዉነት የራቀ ነዉ። እንደ እኔ እምነት፤ ሪክ ማቸር አንድ ትንሽ የአማጽያን ቡድንን እንኳ አልመሩም። ወደ እዚህ ቦታ የመጡት በአጋጣሚ ነዉ፤ ህጉን ደግሞ የሚያረቁት ሌሎች ናቸዉ። እናም ሪክ ማቸርን የሚደግፉ ሌሎች ጥቂት ሰዎች መኖራቸዉ እዉነት ነዉ ግን ሳልቫኪርን እና መንግስታቸዉን በመቃወም በቀጣይ አመፅ ያስነሳሉ ለሚለዉ፤ በቂ ሃይል ስለሌላቸዉ እዉነት አይደለም። በጦርነቱ የተፈናቀሉ፤ የተቸገሩ እና መግብያ ያጡ ሰዎች አሉ።

እንደዉም የበለጠ የተፈናቃይና የችግረኛ ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል የሚል ስጋት አለኝ»
ሁለቱ የደቡብ ሱዳም ተፋላሚዎች ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ላይ በፊርማ የተኩስ አቁም ዉል ቢፈራረሙም ጦርነቱ አያበቃም ባይኖት ማለት ነዉ።
« በርግጥ ምን አይነት አካሄድ ሊኖረዉ እንደሚችል አላዉቅም። ነገር ግን የመረጃ ልዉዉጥ ችግር አለ፤ በተለይ ወደ ገጠሩ አካባቢ። ከዚያም በላይ የሱዳን ህዝብ ነጻ አውጭ ጦር «SPLA» ለሁለት ተከፍሎአል። ቀደም ሲል ሚሊሽያዉ በአንድ ላይ የሚሰባሰብበት ነበር። የመከፋፈል ችግር እንደሚያጋጥም ቢታወቅም ከሰሜናዊ ሱዳን በሰላም ለመገንጠል ሲባል አንድነት ፈጠሩ። እና አሁን የፈነዳዉ ዉጥረትየቀላቀለ አመፅ ፤ እጅግ ጥልቅ የሆነ ክፍፍል እንዳለ ያሳየናል»
ታህሳስ አጋማሽ በጀመረዉ የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ የሰብዓዊ ጥሰት እንደነበረ ዘገባዎች ይፋ አድርገዋል። እና ታድያ ትናንት ምሽት በተፈፀመዉ ዉል ወንጀለኞችን ለፍርድ እንደሚቀርቡ ስምምነት ተደርሶአል?» ሌላዉ ለሱዳን ጉዳይ ምሁሩ ኤሪክ ሪቬስ የቀረበ ጥያቄ ነበር ።
« ለዚህም ጥያቄ አዎንታ መልስ ብሰጥ ደስ ባለኝ። ምክንያቱም ጁባ ላይ ያለዉ መንግስት ማንኛዉንም ሰዉ ወደ ህግ ቦታ እንዲሄድ ፈቃዱ አይደለምና ነዉ። ችግሩ የሚታይበት ቦር፤ ማላካል፤ ወይም ቢንቱ አካቢቢን መጥቀስ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ሲቢሉ ህዝብ ላይ እጅግ ከፍተኛ የጅምላ ጭፍጭፋ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት መካሄዱን አይተናል። ባለፈዉ ስድስት ሳምንት በጦርነቱ በግፍ ስለፈሰሰዉ ደም ደቡብ ሱዳም በህግ ለመዳኘት አቅሙ አይኖራትም»
እንደርሶ ግምት የሰላም ስምምነቱን በሂደት ተግባራዊ ለማድረግ የደቡብ ሱዳን መፈታት ያለበት የረጅም ግዜ ችግር ምን ሊሆን ይችላል፤
«ሶስት ዋና አስፈላጊ ነገሮች አሉ። የሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ወዳጅ አንድ ዓለም አቀፍ አደራዳሪ መፍትሄ እንዲፈልግ ማድረግ ሌላዉ፤ መንግስትን በሙስና ውጥንቅጥ ዉስጥ የዘፈቀዉ፤ የነዳጅ ንግድ በግልጽ ስራ እንዲታይ። ሁለተኛዉ የደቡብ ሱዳን

መንግስት የትክክለኛ መንግስት አቋምን መያዝ ይኖርበታል። በአሁኑ ወቅት ግን እየታየ ያለዉ የጎሪላ እንቅስቃሴ ነዉ፤ ማለት የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጭ ጦር አይነት እንቅስቃሴ። መንግስት አሁን እንደሚታየዉ አይነት አቋም ሳይሆን ይበልጥ ዲሞክራሲያዊ መዋቅር መያዝ ይኖርበታል።»
በማሳቹሲትስ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዩንቨርስቲ የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ጉዳዮችን አዋቂ ፕሮፊሰር ኤሪክ ሬቨስ በሱዳን ለ14 ዓመታት ኖረዉ ምርምርና ጥናት አድርገዋል።

የደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ዉልና ዩናይትድ ስቴትስ

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላት ተወካዮች ትናንት አዲስ አበባ ዉስጥ ያደረጉትን የተኩስ አቁም ሥምምነት የተለያዩ ማሕበራትና ሐገራት ደግፈዉታል።ድጋፋቸዉን ቀድሞዉ ከገለፁት አንዷ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ጀምሮ ያሉ የሐገሪቱ ባለሥልጣናት ባወጡት መግለጫ ተፋላሚዎች ስምምነቱን ገቢር እንዲያደርጉ አደራ ብለዋልም።ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ተገንጥላ የራስዋን መንግሥት እንድትመሠረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጋለች።ያሁኑን የደቡብ ሱዳኖችን የርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ በተደረገዉ ጥረት ግን ብዙም አልተሳተፈችም የሚል ትችት ሲሰነዘርባት ነበር።ሥምምነቱንና የአሜሪካኖችን አቋም በተመለከተ የዋሽግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግረነዋል።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic