የደቡብ ሱዳን ማስተባበያ  | አፍሪቃ | DW | 17.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ማስተባበያ 

ሦስቱ ሀገራት ኢትዮጵያን የሚደግፈውን የሱዳን መንግሥት ለመገልበጥ ለሚታገሉ ታጣቂዎች ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ለመክፈት መስማማታቸውን ሱዳን ትሪብዩን ጋዜጣው ዘግቧል። ደቡብ ሱዳን ግብጽ እና ዩጋንዳ ለሱዳን ተቃዋሚዎች ማሰልጠኛ ጣቢያ ለማቋቋም ተስማምተዋል ተብሎ የቀረበውን ዘገባ ደቡብ ሱዳን አስተባበለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

የደቡብ ሱዳን ማስተባበያ

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒትየ ሞርጋን አዲስ አበባ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተሰራጨው ዜና ሀሰት ነው ብለዋል። ሱዳን ትሪብዩን የተባለው ጋዜጣ  ባለፈው ሳምንት  ባወጣው ዘገባ የሦስቱ ሃገራት መሪዎች፣ በአባይ ወንዝ ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የምትገነባውን ኢትዮጵያን የሚደግፈውን የሱዳን መንግሥት ለመገልበጥ ለሚታገሉ ታጣቂዎች ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ለመክፈት መስማማታቸውን ተችዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል ።   

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ


ኂሩት መለሰ 

ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic