የደቡብ ሱዳን መኮንኖች የአዲስ አበባ ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 19.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የደቡብ ሱዳን መኮንኖች የአዲስ አበባ ጉባኤ

የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና አማፂያን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ካለፈው ሳምንት እሁድ አንስቶ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት የሰላም ንግግር ፤ ትናንት አርብ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 06:20

የጦር መኮንኖቹ ለውይይት ከቀረቡት ሰባት ጉዳዮች በአንዱ ብቻ አለመስማማታቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል። መኮንኖቹ ያልተስማሙት ዋና ከተማይቱን ጁባን ጨምሮ የሌሎች ከተሞችን ፀጥታ በሚያስከብር ፖሊስ አወቃቀር ላይ ነው። በስምምነቱ መጨረሻ ላይ የተዘጋጀውን ውል የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ወገኖች እና ሌሎች የአማፂያን መኮንኖች ቢፈርሙም፤ ከአማፂያኑ መካከል የአንዱ ቡድን ሳይፈርም ቀርቷል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic