የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ዉሳኔ: አዉሮጳ ሕብረትና ኢጋድ | ኢትዮጵያ | DW | 23.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ዉሳኔ: አዉሮጳ ሕብረትና ኢጋድ

የአውሮፓ ኅብረት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ፣በብራሰልስ ውስጥ ባደረጉት ጉባዔ፣ ለደቡብ ሱዳን ህዝበ- ውሳኔ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን የገለጡ ሲሆን፣ የኢጋድ አባል መንግሥታት መሪዎችም፣ አንዳንድ ሳንኮች ይወገዱ ዘንድ ከሱዳን መሪዎች---

default

የሕዝበ-ዉሳኔ ምዝገባ

የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ዉሳኔና አዉሮጳ ሕብረት


የአዉሮጳ ሕብረት የሱዳን መንግሥትና የቀድሞዉ የደቡብ ሱዳን ነፃ አዉጪ ንቅናቄ ከአምስት አመት በፊት የተፈራራሙትን ሥምምነት ገቢር ለማድረግ ከእንግዲሕ የሚያደርጉትን ድርድር ለማገዝ ዝግጁነኝ አለ።የሕብረቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት ትናንት በጉዳዩ ላይ ከተነጋገረ በሕዋላ ባወጣዉ መግለጫዉ በመጪዉ ጥር ደቡብ ሱዳን ዉስጥ የሚደረገዉን ሕዝበ ዉሳኔ የሚታዘብ ቡድን እንደሚልክም አስታዉቋል።መገለጫዉ መሠት ሕብረቱ የደቡብ ሱዳንንም ሆነ የዳርፉርን ችግር ለማስወገድ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ወገኖች ጋር ተባብሮ ይሠራል።

---------------------

የአውሮፓ ኅብረት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ፣በብራሰልስ ውስጥ ባደረጉት ጉባዔ፣ ለደቡብ ሱዳን ህዝበ- ውሳኔ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን የገለጡ ሲሆን፣ የኢጋድ አባል መንግሥታት መሪዎችም፣ አንዳንድ ሳንኮች ይወገዱ ዘንድ ከሱዳን መሪዎች ዖማር አል በሺርና ሳልቫ ኪር ጋር መክረዋል።

ገበያዉ ንጉሴ

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች