የደርግ ዘመን ባለሥልጣናት መፈታት | ኢትዮጵያ | DW | 05.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የደርግ ዘመን ባለሥልጣናት መፈታት

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው 23 ባለሥልጣናት መካከል፣16 ቱ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል። ባለሥልጣናቱ የተፈቱት፤ በሃይማኖት ተጠሪዎች ጥረት ነው ተብሏል።

default

በደርግ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው በከፊል

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፤ «የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል » ብሎ የከሠሣቸው በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው 23 ባለሥልጣናት መካከል፣16 ቱ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል። ባለሥልጣናቱ የተፈቱት፤ በሃይማኖት ተጠሪዎች ጥረት ነው ተብሏል። የሃይማኖት ሰዎች፤ ከወዲሁ፤ ፍትኅና ርትእ እንዲኖር፤ ትኩረት ሰጥተው መሥራት፤ ሰዎች አላግባብ፤ በግፍ እርምጃ እንዳይታሠሩ ፤ እንዳይገደሉ፤ ማስተማር፤ ዕርቀ-ሰላም እንዲወርድ መጣር ፤ መንፈሳዊ ተልእኮአቸው እንደሚያስገድዳቸው የታወቀ ነው። 20 ዓመት በእሥራት ላይ ከቆዩ በኋላ፤ ስለተፈቱት የደርግ ባለሥልጣናት ፤ ታደሰ እንግዳው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

Audios and videos on the topic