የደርባኑ ዓለም ዓቀፍ የኤድስ ጉባኤ ፍጻሜ | አፍሪቃ | DW | 22.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የደርባኑ ዓለም ዓቀፍ የኤድስ ጉባኤ ፍጻሜ

ይኽው ጉባኤ ከፀረ ኤች አይቪ ኤድስ ዘመቻ መዳከም አንስቶ ፣ እስከ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሐኖቶች ዋጋ መናር ድረስ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:37

የደርባኑ የኤድስ ጉባኤ ፍጻሜ


ከዚህ ሳምንት ሰኞ አንስቶ ደርባን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው 21 ኛ ዓለም ዓቀፍ የኤድስ ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ሳይንቲስቶች ፣ ፖሊሲ አውጭዎች ፣ የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የሚጥሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተወካዮች የተካፈሉበት ይኽው ጉባኤ ከፀረ ኤች አይቪ ኤድስ ዘመቻ መዳከም አንስቶ ፣ እስከ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሐኖቶች ዋጋ መናር ድረስ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል ። ጉባኤው በተካሄደባት በደቡብ አፍሪቃ በየሳምንቱ እድሚያቸው ከ15 እስከ 24 የሚሆን ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ወጣት ሴቶች በኤች አይ ቪ ኤድስ ይያዛሉ ። ከ18 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ስለተገኙበት ስለዚህ ጉባኤ ጉባኤው ሂደት እና ከጉባኤው ፍፃሜ ምን እንደሚጠበቅ የጆሃንስበርጉን ተባባሪ ዘጋቢያችንን መላኩ አየለን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። በቅድሚያ ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገረባቸውን ዐበይት ጉዳዮች ይነግረናል ።

መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic