የደራሲዉ የብዕር ትግል | ባህል | DW | 04.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የደራሲዉ የብዕር ትግል

«አፍሪቃ ህዝብ ነዉ። አፍሪቃ ማለት በችግር ዉስጥ ያለ ብቻ ማለት አይደለም። ይህንን ካልተረዳን ደግሞ የሚደረገዉ ርዳታ ተገቢዉን ስኬት ሊያመጣ አይችልም ሰብዓዊነትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል አለብን። »

default

ቺኑአ አቼቤ

ታዋቂዉ ናይጀርያዊዉ ደራሲና የፖለቲካ ሃያሲ ቺኑአ አቼቤ በጎ,አ 2002 ዓ,ም ጀርመንን በጎበኘበት ወቅት አዉሮጳዉያን ስለአፍሪቃ የሚያስቡትና የሰሙትን ስር የሰደደ ትክክለኛ ያልሆነን አመለካከት እንዲቀየሩ ባደረገዉ ንግግር እንዲህ ሲል አሳስቦ ነበር።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በስነ-ጽሑፍ ስራዉ በዓለም አድናቆትን ያገኘዉ ናይጀሪያዊ ደራሲ ፕሮፊሰር ቺኑአ አቼቤ በ82 ዓመቱ ባለፈዉ ሰምወን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይትዋል። ደራሲዉ በስነ ጽሁፍ ስራዎቹ ብቻ ሳይሆን የሚታወቀዉ በጋዜጠኝነት አስተማሪነት እና በጠንካራ ሃያሲነቱም ነበር። የናጀርያዊዉ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች በዓለም አገራት ቋንቋዎች ተተርጉመዉ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለስነ-ጽሁፍ ማስተማርያነትም ጥቅም ላይ ዉለዋል። በዕለቱ ዝግጅታችን የፕሮፊሰር ቺኑአ አቼቤን ስራዎች እናያለን የሀገራችንን የስነ-ጽሁፍ ይዘት የሚነግሩንን ምሁራን ጋብዘናል፤

Nigerian author Chinua Achebe, right, receives the German Booksellers Peace Prize from the President of the German book trade association, Dieter Schormann, Sunday, Oct. 13, 2002, in the Paulschurch in Frankfurt, Germany

በጎ 2002 በጀርመን ታዋቂዉን የስነ-ጽሁፍ የሰላም ሽልማት አግኝቶአል

ባለፈዉ ሰምወን በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዉ ናይጀርያዊዉ የፖለቲካ ሃያሲና የስነ-ጽሁፍ ሰዉ ፕሮፊሰር ቺኑአ አቼቤ በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር 2002 ዓ,ም በብዕሩ ሳይፈራና ሳያፍር በሃቀኝነት ለአንባብያን ባቀረበዉ ጽሁፉ በጀርመን ታዋቂዉን የስነ-ጽሁፍ የሰላም ሽልማት አግኝቶአል።

ታዋቂዉ ናይጀርያዊ ደራሲ በጎ,አ 1930 ዓ,ም ህዳር ወር ላይ በደቡብ ምስራቅ ናይጀርያ ተወለደ በ 28 ዓመቱ በዓለም የስነ-ጽሁፍ መድረክ ያስተዋወቀዉን „Things Fall Apart“ የተሰኘዉን የመጀመርያ ድርሰቱን ለአንባብያን አቀረበ። ይህ የስነ-ጽሁፍ ስራዉ ደራሲዉን እዉቅና ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ ዘመናዊ የስነ-ጽሁፍ አባት አሰኝቶታል፤ ይህኑ በርካታ ምዕራባዉያንም መስክረዉለታል።

የደራሲ ቺኑአ አቼቤ ስራዎች አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አፍሪቃን ስነ-ጽሁፍ ማስተማርያ ነዉ ያሉን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የነበሩትና አሁንም በአንዳንድ ትምህርቶችን እንደሚሰጡ የነገሩን አንጋፋዉ ደራሲ አያልነህ ሙላቱ፤ በሀገራችን የታወቀ ደራሲ ነዉ ሲሉ ገልጸዉልናል። በድርሰቱም ትምህርት ይሰጣል።

18.03.2013 DW online Karte Nigeria Kano eng

ናይጀርያ

ከአፍሪቃ ደማቅ አሻራቸዉን ከተዉት ፀሃፍት መካከል አንዱ የሆነዉ ናይጀርያዉ ቺኑአ አቼቤ ወደ ሥነ ፅሁፍ ህይወት ለመግባት መነሻዉ የነጮች የበላይነት ነበር። በተለይም የአፍሪቃዉያን ታሪክ እና ማንነት በአዉሮጳዉያን ደራስያን መፃፍ እንደማይገባዉ ጠንካራ እምነት እንደነበረዉ ታሪኩ ያወሳል። ምክንያቱም ምዕራባዉያን ስለአህጉሪቱ የሚጽፉት ታሪክ ማንነትን በአግባቡ የማይገልጽ እና የተዛባ ምስል የሚፈጥር መሆኑን ያምናል። ለዚህም በዓለም አንባብያን ዘንድ አድናቆትን ያገኘበት „Things Fall Apart“ የተሰኘዉ የመጀመርያ ድርሰቱ ጥሩ ማስረጃ መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ። ደራሲ ቺኑአ አቼቤ በዚህ ስራዉ በ 19 ምዕተ ዓመት የአዉሮጳ ሚሲዮናዉያን ወደ አፍሪቃ ይዘዉ የገቡትን ለዉጥ ለመቀበል አንድ ትልቅ እና ጠንካራ አፍሪቃዊ ያገጠመዉን እጣ ፈንታ ይተርካል። ድርሰቱ በተለይ የአዉሮጳዉያንን ቅኝ ግዛት ከአፍሪቃዉያን አስተሳሰብ አንፃር በግልጽ በማስቀመጡ እዉቅናን አግኝቶለታል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና በዩኤስ አሜሪካ በሚገኝ ዩንቨርስቲ የአፍሪቃ ስነ-ጽሁፍንና ፤ በስነ-ቋንቋ ሳይንስ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር ሃይሉ አርዓያ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ የማደንቀዉ ደራሲ ነዉ በኢትዮጵያም ሆነ በዩኤስ አሜሪካ ኮሌጆች በመጻህፉ አስተምሪአለሁ!

Der nigerianische Schriftsteller Chinua Achebe auf einem Archivbild vom 13. Mai 1988. Der Friedenspreis des Deutschen Buchhandels geht in diesem Jahr an Achebe. Das teilte der Boersenverein des Deutschen Buchhandels mit, wie am Montag, 3. Juni 2002, gemeldet wurde. (AP Photo/Bill Cramer, file) --zu APD2883--

ቺኑአ አቼቤ

የቺኑአ አቼቤ ድርሰት ቅኝ ግዛት አልያም አጽናፋዊዉ ትስስር ማለት ግሎባላይዜሽን ያመጣዉን ለዉጥ ለመገንዘብ ወይም ለማጥናት ለሚፈልጉ አፍሪቃዉያን የስነ-ጽሁፍ ባለሞያዎች ፈር ቀዳጅ ነዉ ሲሉ ጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ እና የመፅሃፍት ሽያጭ ጠበብት ሆልገር ኤሊንግ ተናግረዉላቸዋል።

ደራሲ ቺኑአ አቼቤ እስከ 1966 ዓ,ም በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ፤ በናይጀርያ በጋዜጠኝነት አገልግለዋል፤ የመጀመርያ ስነ-ጽሁፉን ተከትሎ ሶስት ድርሰቶችን ጽፈዋል። ፧ከዝያም በናይጀርያ የደራሲ ቺኑአ አቼቤ ግዛት ሆነችዉ ኢግቦ ለመገንጠል ከጎርጎረሳዉያኑ 1967 እስከ 1970 ዓ,ም ለአራት አመታት በተደረገዉ አስከፊዉ የቢያፍራ የእርስ በርስ ጦርነት በሚሊዮን ህዝብ አልቆ ኢቦስ ጎሳዎች ሪፑብሊክ ቢያፍራ ሲሉ ነጻነታቸዉን ያዉጃሉ። በዝያ ወቅት ደራሲ ቺኑአ አቼቤ ቢያፍራ በዉጭ ሀገራት እንደ ሀገር እዉቅና እንድታገኝ የሰላም ጥያቄን በማቅረብ በዉጭ አገራት አገልግሎአል። ግን በጎርጎረሳዉያኑ 1970 ዓ,ም ግልበጣዉን ያደረጉት የመጨረሻዎቹ ወታደሮች እጃቸዉን ከሰጡ በኋላ ቢያፍራ በናይጀርያ መንግስት ቁጥጥር ይገባል። ከዚህ ጦርነት በኋላ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ በድርሰቱ የጦርነቱን መንስኤና በጦርነቱ የነበረዉን ወንጀል ለማወቅ እና ይፋ ለማድረግ ትግሉን ይጀምራል። ናይጀርያ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ልትወጣ ሁለት አመት ሲቀራት ለአንባብያን ይፋ የሆነዉ „Things Fall Apart“ የተሰኘዉ የአቼቤ ድርሰት የነጻነትን ጭብጥ ያዘለ ነዉ። ድርሰቱ አጉልቶ ከሚያወጣቸዉ ነገሮች ይላሉ ዶክተር ሃይሉ አርአያ ፤ አንዱ በአፍሪቃዉያን እና በኮልያኒስቶች መካከል ያለዉን የተለያየ አስተሳሰብ አጉልቶ ያወጣል።

Der Sitz der Economic Community of West African States, ECOWAS, aufgenommen am 02.11.2012 in Abuja in Nigeria.

የኢኮዋስ ዋና መቀመጫ በአቡጃ መዲና

ማንኛዉም ጥሩ ታሪክ ወይም ልቦለድ በሚኖረዉ ስነ-ጽሁፋዊ ተልዕኮ ጠንካራ መልክትን ማዘል ይገባዋል የሚል አቋም የነበረዉ ደራሲ አቼቤ በቅኝ ግዛት ቋንቋ ብሎ በሚጠራዉ እንግዚዘኛ ቋንቋ ረጃጅም ድርሰቶችን ለአንባብያን በማቅረብ ግንባር ቀደሙ አፍሪቃዊ እንዲሆን አድርጎታል። ቺኑአ አቼቤ በጎአ 2007 ዓ,ም “Man Booker International Prize“ የተሰኘዉን በብሪታንያ ለእንግሊዘኛ ምርጥ ድርሰቶች የሚሰጠዉን ዓለማቀፍ ሽልማት አግኝተዋል። ደራሲ አያልነህ ሙላት ቺኑአ አቼቤ የአፍሪቃን ስነ-ጽሁፍ ከዓለም ጋር ያቆራኘ ጸሃፊም ነዉ ብለዋል።

ናይጀርያ ከቅኝ ግዛት ተላቃ በአገርዋ ተወላጅ መተዳደር ከጀመረች በኋላም አቼቤ ከአገሩ ፖለቲከኞች ጋር የነበረዉ ግንኙነት እጅግ ቀዝቃዛ ነበር። በናይጀርያ የሚታየዉ የአስተዳደር መጓደል እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲሁም ሙስና እና የመብት ጥሰትን በመቃወም አቼቤ በአደባባይ ትችት በማድረጉ ይታወሳል። በናይጀርያ መንግስት ለሽልማት በተደጋጋሚ ቢታጭም አልፈልግም ብሎ ሽልማቱን አልተቀበለም። እንደ አቼቤ « የናይጀርያ መሰረተ ልማት ሳይሟላ ዘጎችዋ ሳይደሰቱ የዲሞክራሲ ጥቅሙ አይታየኝም ሲል በጎአ 2007 ዓ,ም አለማቀፉን ሽልማት በወሰደ ግዜ መናገሩ ተገልጾአል። አፍሪቃዉያኑ ጻህፍት ምንም እንኳ በእንግሊዘኛ ይጻፉ እንጂ መሰረት የሚያርጉት የአገራቸዉን ባህል ነዉ ሲሉ ደራሲ አያልነህ ሙላት ተናግረዋል

በተለያዩ ዓለማት በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መጽሃፉ ለማስተማርያነት የተመረጠበት ዋና ምክንያት ይላሉ ዶክተር ሃይሉ አርዓያ በመቀጠል፤ ድርሰቱ የአፍሪቃዉያኑን ባህል ይስላል በሁለተኛ ደረጃ በአፍሪቃ የነበሩትን አዉሮጳዉያን ይገልጻል።

እንደ በርካቶች እምነት የደራሲ ቺኑአ አቼቤ ድርሰት የኖቤል ሽልማትን የሚሰጡት ናቸዉ፤ ግን ድርሰቶቹ ለኖቤል ሽልማቱ ብቁ መሆን አለመሆናቸዉ ድርድር ጠረቤዛ ላይ ቀረቡ እንጂ ኖቤል ሽልማትን አላገኘም። ከሀገሩ ከወጣበት ከጎአ 1970 ዓ,ም በኋላ ወደ አገሩ የተመለሰዉ በጣም ለጥቂት ግዝያት መሆኑ ተጠቅሶአል። በርካታ ህይወቱን በዪኤስ አሜሪካ ያሳለፈዉ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ bb,ፕሮፊሰርነት ማዕረግ ስለአፍሪቃ ስነጽሁፍ አስተምሮአል። በጎአ 1990 በ60 ዓመቱ በደረሰበት ከፍተኛ የሆነ የመኪና አደጋ አካሉ መታዘዝ ባለመቻሉ በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ዋለ። ባለፈዉ የጎአ 2012 ዓ,ም ፕሮፊሰር አቼቤ በናይጀርያ ከፍተኛ ክርክርን ያስነሳ „ There Was A Country” የተሰኘዉን የመጨረሻ ድርሰቱን ለአንባብያን አቅርበዋል። ድርሰቱ የቢያፍራ ጦርነትን ግፍ ያወሳል። በናይጄርያ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን በብዕሩ ሲታገል የኖረዉ የስነ-ጽሁፍ ሰዉ በተለይ”Things Fall Apart”የተሰኘዉ ድርሰቱ በዓለም ዙርያ በሚነገሩ ከ50 በላይ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከ 8 ሚሊዮን በላይ ቅጅዎች ተሸጦአል። በዚህም የቺኑአ አቼቤ የስነ-ጽሁፍ ስራ በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመና የተሸጠ የመጀመርያዉ አፍሪቃዊዉ ደራሲ የመጀመርያዉ ያደርገዋል።

GettyImages 84357511 Nigerian writer, 70, Chinua Achebe is pictured on January 19, 2009 during a welcoming ceremony at Nnamdi Azikiwe International Airport in Abuja upon his return to Nigeria for the firrst time in over 10 years. Achebe, whose most famous work is 1958's 'Things Fall Apart,' is a literature professor at Bard College in New York state. AFP PHOTO / Abayomi Adeshida (Photo credit should read ABAYOMI aDESHIDA/AFP/Getty Images)

ቺኑአ አቼቤ

ባለትዳር የአራት ልጆች አባት እንዲሁም አያት የነበረዉ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ፤ አፍሪቃ አህጉርን ያስጠራ ለበርካታ ጻህፍት አርአያ የሆነ ታላቅ አፍሪቃዊ ደራሲ ነበር፤ የአፍሪቃ ህብረት ግንቦት ወር ላይ በሚያከብረዉ ሃምሳኛ አመት የምስረታ በዓል መታሰብያ እንደሚዘጋጅለት ዘገባዎች ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያላት ሃያስያን እን ጻህፍ የሚስተካከል ባይኖርም ጻህፍቶቻችን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ ደራሲ አያልነህ ሙላቱ ይገልጻሉ፤ ቅኝ ግዛትን በብዕሩ ስለታገለዉ እዉቅ ናይጀርያዊ ደራሲን የስነጽሁፍ ስራዎች የቃኘንበትን የዕለቱን ዝግጅታችን እዚህ ላይ እና ጠናቅቃለን። ለቅንብሩ አዜብ ታደሰ ፤ ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic