የዮናታን ተስፋዬ ፍርድ መቅለል | ኢትዮጵያ | DW | 27.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዮናታን ተስፋዬ ፍርድ መቅለል

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈባቸውን የ6 ዓመት ከ6 ወር የእሥር ውሳኔ ወደ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ሌላ የፀረ ሽብርን ሕግ መሠረት በማድረግ የቀረበባቸውን ክስም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉ ገደቦችን በመተላለፍ በሚል ክስ አቅልሎታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:33

አቶ ዮናታን የተላለፈባቸው ፍርድ እና የተከሰሱበት የወንጀል ጭብጥ ቀለለ።

ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ የተላለፈባቸውን ፍርድ እና የተከሰሱበትን የወንጀል ጭብጥ አቀለለ። የአቶ ዮናታንን ይግባኝ የተቀበለው ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈባቸውን የ6 ዓመት ከ6 ወር የእሥር ውሳኔ ወደ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝቅ  አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ሌላ የፀረ ሽብርን ሕግ መሠረት በማድረግ የቀረበባቸውን ክስም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉ ገደቦችን በመተላለፍ በሚል ክስ አቅልሎታል። አቶ ዮናታን የኢትዮጵያን መንግሥት የሚተች ጽሁፍ በፌስቡክ አሰራጭተዋል በሚል ከታኅሳስ 2008 ዓ,ም አንስቶ በእሥር ላይ ናቸው። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጠበቃቸውን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ

Audios and videos on the topic