የያሲር አረፋት አሟሟትና ምርመራዉ | ዓለም | DW | 27.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የያሲር አረፋት አሟሟትና ምርመራዉ

አረፋት በጠና በታመሙበት ወቅት ይጠቀሙበት በነበረዉ የጥርስ ቡሩሽና ይጠመጥሙት በነበረዉ ካፍያ ላይ በተደረገዉ ምርመራ ፖልኒየም ሁለት መቶ የተሰኘዉ ገዳይ መርዛማ ንጥረ ነገር ተገኝቶበታል።የመርዙ መገኘት በፍልስጤማዉያን ዘንድ አረፋትን ያስገደለችዉ እስራኤልነች የሚል ጥርጣሬ አስከትሏል

Palestinian leader Yasser Arafat pauses during an emergency cabinet session, at his compound, in the West Bank town of Ramallah in this Saturday, Oct. 2, 2004 file photo. Late Wednesday, Oct. 27, 2004, Arafat's health deteriorated and his doctors rushed to his room to examine him, an official in Arafat's office said. Soon after, Palestinian Prime Minister Ahmed Qureia and former Prime Minister Mahmoud Abbas were summoned to Arafat's compound, the official said. (AP Photo/Muhammed Muheisen)

አረፋት

የቀድሞዉ የፍልስጤም ራስ ገዝ መስተዳድር ፕሬዝዳት የያሲር አረፋት አሟሟትን ለማጣራት የሚደረገዉ ምርመራ ዛሬም ከስምንት ዓመታት በሕዋላ አልተጠናቀቀም።አረፋት በጠና በታመሙበት ወቅት ይጠቀሙበት በነበረዉ የጥርስ ቡሩሽና ይጠመጥሙት በነበረዉ ካፍያ ላይ በተደረገዉ ምርመራ ፖልኒየም ሁለት መቶ የተሰኘዉ ገዳይ መርዛማ ንጥረ ነገር ተገኝቶበታል።የገዳዩ መርዝ መገኘት በፍልስጤማዉያን ዘንድ አረፋትን ያስገደለችዉ እስራኤልነች የሚል ጥርጣሬ አስከትሏል። ሐኪሞች እንደሚሉት ግን በአረፋት ንብረት ላይ መርዛማ ንጥረ ነገር መገኘቱ ለፍልስጤሙ አንጋፋ መሪ ሞት ምክንያት መሆኑን አያረጋግጥም።በዚሕም ምክንያት የሲዊስ፥ የፈረንሳይ፥ የሩሲያና የፍልስጤም ሐኪሞች ዛሬ የአረፋትን ቀብር ከፍተዉ ከአረፋት አካል ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ይጠቅማል ያሉትን ናሙና ወስደዋል።ሥለ ጉዳዩ የይፋዉን ወኪላችንን ግርማዉ አሻግሬን ስቱዱዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ግርማዉ አሻጋሪ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic