የዩጋንዳ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ | ኢትዮጵያ | DW | 19.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዩጋንዳ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

በምስራቅ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዩጋንዳ ትናንት ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ሰባት የተቃዋሚ ወገን ዕጩዎች ዩጋንዳን ላለፉት ሀያ አምስት ዓመት በመሩት የስድሳ ስድስት ዓመቱ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አንጻር ተወዳድረዋል።

default

ከሰባቱ መካከል ዋነኛው የፕሬዚደንት ሙሴቬኒ ተፎካካሪ የሚባሉት የፎረም ፎር ዴሞክራቲክ ቸንጅ ፓርቲ ዕጩ ኪዛ ቢሴጌይ ናቸው። በምርጫው ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ እንደሚያሸንፉ በሀገሪቱ የወጡ የህዝብ አስተያየት መመዘኛ መዘርዝሮች ጠቁመዋል። የተቃዋሚው ወገን ዕጩ ቢሴጌይ ግን ምርጫው ሊጭበረበር እንደሚችል ከወዲሁ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ቢሴጌይ በአስመራጩ ኮሚሽን ላይ እምነት እንደሌላቸው ነው ያስታወቁት።

አርያም ተክሌ
መስፍን መኮንን