የዩጋንዳ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢልና የቴክኖሎጂ ይዞታ በአፍሪቃ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 10.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የዩጋንዳ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢልና የቴክኖሎጂ ይዞታ በአፍሪቃ

ከአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፣ ሞሮኮ፣ ለኃይል ምንጭ ፣ ከነዳጅት ዘይት ይልቅ ለፀሐይ ሙቀትና ብርሃን የላቀ ግምት የሰጠችበት እንቅሥቃሤ በአወንታዊነት ሲጠቀስ፣ ዩጋንዳ ለተፈጥሮ ተስማሚ ነው ያለችውን በኤሌክትሪክ የሚሽከረከር አውቶሞቢል መሥራት ብቻ

ሳይሆን፤ በመላው ምሥራቅ አፍሪቃ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ቆርጣ መነሳቷ ይበል የሚያሰኝ ሆኗል።በዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ቅንብራችን፣ በዩጋንዳ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፕሮጀክትን መነሻ በማድረግ በሥነ ቴክኒክ ዝውውር ወይም ሽግግር ላይ ላይ ይሆናል የምናተኩረው።

በዓለም ዙሪያ ፤ ከ 25 ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች የተውጣጡ ተማሪዎች ፤ እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም፤ በዩናይትድ ስቴትሱ ማሳቹሰትስ የሥነ ቴክኒክ ተቋም፣ በኤሌክትሪክና በሌላም አማራጭ ኃይል የሚሠራ የአውቶሞቢል ንድፍ እንዲያቀርቡ ተመድበው ፤ ከ 3 ዓመት በኋላ፤ በፀሐይ ኃይል፣ከአትክልት ፤ ፍግና ከመሳሰለው በሚነጠር ነዳጅ የሚነቀሳቀስ ተሽከርካሪ ሠሩ።ከሠሪዎቹ መካከል የዩጋንዳውያን የ ማካሬሬ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ነበሩበት። በዚህ ውጤት የተበራታቱት ጥቂት ዩጋንዳውያን ናቸው እንግዲህ ፣ እ ጎ አ በ 2009 በጠቅላላ ከ 25 የማካሬሬ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በአፍሪቃ ምድር በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀስ የአውቶሞቢል ንድፍ አውጥተው የሠሩት።

«ኪራ ኢ ቪ» ትሰኛለች፣ ንድፍ ወጥቶላት የተሠራችውና 2 ሰዎች የምታሳፍረው ተሽከርካሪ! የተሠራችውም፤ በከተሞች አገልግሎት እንድትሰጥ ታስቦ ነበረ። ሞተሩን ፣ የማካሬሬ ዩንቨርስቲ ኢንጂኔሮች ናቸው የሠሩት።አንዳንድ የአውቶሞቢሏ ክፍሎች ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የተገኙ ነበሩ። የአድካሚው ሥራ ውጤት ያረካቸው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ፣ የፕሮጀክቱ ተጠሪ በመሆን ሥራው እንዲቀጥል አበረታቱ። «ኪራ ኢ አውቶሞቢል»፤ ምሥራቅ አፍሪቃ፤ በግብርናና ከብት ርባታ ብቻ የታወቀ አለመሆኑን ማሥመስከር አለባት ተባለ። ዩጋንዳ ከእንግዲህ የ 3ኛ ዓለም አካል ሆና አትኖርም ያለው ያገሪቱ መንግሥት ፣ ለአውቶሞቢል ፋብሪካ ፣ በመቶ ሚሊዮኖች ዩውሮ የሚገመት ገንዘብ መደቧል። አነስተኛ አውቶሞቢል ብቻ ሳይሆን ፤ በኤልክትሪክ የሚነቀሳቀስ አውቶቡስም በዩጋንዳ ልጆች ተሠርቷል ። እ ጎ አ ከ 1918 ዓ ም ጀምሮ ፋብሪካው ለገበያ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ን ያቀርባል። የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ፖል ሙሳሲዚ --

«ይህ ሞተሩን የሚያሠራው ነው። --ሞተሩ፤ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ወደ «መካኒካል» ኃይል ይለውጠዋል።ይህ ነው ተግባሩ። አጠገቡ የፀሐይ ኃይል በመሳብ ፣ ባትሪው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሞላ የሚያደርጉ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት የሚያጠራቅሙ መሣሪያዎች አሉ።ለመመርመር የምንሞክረው፣ ዩጋንዳ በምድር ሰቅ የምትገኝ ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ቢያንስ የ 8 ሰዓት የፀሐይ ብርሃን እንደምታገኝ ነው። እናም ይህ የፀሐይ ብርሃን ለህዝብ ማጓጓዣ አገልግሎት እስከምን ድረስ አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚችል ለማወቅ እንፈልጋለን።»

በከርሰ-ምድሯ ሰፊ የነዳጅ ሃብት ማግኘቷን ያረጋገጠችው ዩጋንዳ ፣ ካሁኑ ለሰውም ለተፈጥሮም የሚበጅ ሥነ ቴክኒክ መምረጧ እሰየው የሚያሰኝ ሊሆን ይችላል።

እንደ ዩጋንዳ በሌሎች የአፍሪቃ ዩንቨርስቲዎች ያለው የፈጠራ ስሜትና እንቅሥቃሤ እንዴት ይሆን? ለምሳሌ ፤ 40 ሺ ተማሪዎች ባሉት የስዋኔ(ፕሪቶሪያ )የቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ! በዚያ የሚገኙት ፕሮፌሰር ዶ/ር ማሞ ሙጬ--

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic