የዩጋንዳዉ አማፂ ቡድን ግፍ | አፍሪቃ | DW | 21.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዩጋንዳዉ አማፂ ቡድን ግፍ

።«ልጁ ወላጆቹን እንዲገድል ይታዘዛል።ልጁ ትዕዛዙን ሲፈፅም ወድሞቹ፤የአክስት አጎት ልጁቹ እና ሌሎች ዘመዶቹም እንዲያ ይገደዳሉ።ከዚያ በሕዋላ ገዳዩን ወላጆቹን ወይም ዘመዶቻችንን የገደለ እያሉ እረፍት ያሳጡታል።እሱም እነሱም የተሠራዉን አይረሱም

የፈጣሪ መከላከያ ጦር (LRA-በእንግሊዝኛ ምሕጻሩ) የሚያግታቸዉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ዘገባ እንዳመለከተዉ ዩጋንዳን በአሥርቱ የመፅሐፍ ቅዱስ ትዕዛዛት መሠረት ለመግዛት ያለመዉ ጨካኝ ቡድን ባለፉት አሥራ-አንድ ወራት ብቻ 432 የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዜጎችን አፍኖ ወስዷል።በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀለኝነት ተከሶ የሚታደነዉ ጆሴፍ ኮኒ የሚመራዉ ቡድን ከየሥፍራዉ እያፈነ የሚወስዳቸዉ አብዛኞቹ ታዳጊ ወጣቶች ናቸዉ። ክሎታ ዋንጆሒ የዘገበችዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

የአፍሪቃ ሕብረት ጦር እንደሚለዉ ጆሴፍ ኮኒን ለመያዝ ጦሩ ከዘመተ ጀምሮ አሸባሪዉ ቡድን ባብዛኛዉ ዩጋንዳ፤ አልፎ አልፎ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፕብሊክና ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፕክሊክ ዉስጥ-ሰዎችን አካላታቸዉን እየቆራረጠ፤ በየጎጆቸዉ እሳት እየለቀቀ፤ ሲያሰኘዉ በጥይት እየረሸነ-መግደል ማሰቃየቱ ቀንሷል።

የሕብረቱ ጦር የመረጃ አስተባባሪ ሻምበል ሉዊስ ቻርልስ ፤ዩጋንዳ መራሹ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2010 ቡድኑን ማጥቃት ከጀመረ ወዲሕ፤ ቡድኑ አደጋ የማድረስ አቅሙም ተዳክሟ።«ከ2010 ወዲሕ የዉጊያ ሥልታቸዉን ለዉጠዋል።እንደ መደበኛ ቡድን ሆነዋል።አካላት መቆራረጣቸዉን አቁመዋል።የሚገድሉትም ሕልዉናቸዉን ለማስጠበቅ ሲሉ ነዉ።»

የአፍሪቃ ሕብረት ጨካኙን ቡድኑን የሚወጋ አምስት ሺሕ ጦር ለማዝመት ወስኖ ነበር። ዩጋንዳ ሁለት ሺሕዉን ለማዋጣት ቃል ስትገባ፤ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፤ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፤ እና ደቡብ ሱዳን እያንዳዳቸዉ አንዳድ ሺሕ ጦር ያዋጣሉ ነበር-ቃል ተስፋዉ።

አልሆነም።ሁሉም በየራሳቸዉ ችግር ሲወጠሩ ቡድኑን ለመዉጋት የዘመተዉ 1500-የዩጋንዳ፤ 500 የተቀሩት ሐገራት ጦር ብቻ ነዉ።2000 በድምሩi።ሻምበል ቻርልስ እንደሚሉት የጦሩ ቁጥር፤የዘመቻዉ ዉጤትም የተፈለገዉን ያሕል ባይሆንም ዘመቻዉ የቡድኑን አቅም በጅጉ አዳክሞታል።«የቡድኑ አባላት ሰዎችን የሚያግቱት ላጭር ጊዜ ነዉ።ካንድ ሁለት ቀናት በኋላ ይለቋቸዋል።ታጋቾቹን የሚጠቀሙባቸዉም ዕቃ እንዲሸከሙ ነዉ።መንደሮችን አያቃጥሉም።የሚዘርፉትም እራሳቸዉን ለማቆየት ያሕል ብቻ ነዉ።»

የአሸባሪዉ ቡድን ጨካኝ መሪ ግን እስካሁን ያለበት አይታወቅም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናትም በተለይ እገታን በመለከተ ከሻምበሉ መግለጫ ጋር ይቃረናል።ከጥር እስከ እስካሁን በተቆጠሩት አሥራ-አንድ ወራት ዉስጥ ብቻ፤ካንዲት ማዕከላዊ አፍሪቃ ብቻ ከ430 በላይ ወጣቶችን አግቷል።አምና እና ዘንድሮ የታገቱት ወጣቶች ቁጥር ሐቻምና ከታገቱት በጅጉ ጨምሯል።

ታጋቹ ወንድ ከሆነ-በተዋጊነት፤በተሸካሚነት፤በተዋጊ-አዋጊዎች ተላላኪነት ያገለግል።ሴቶችና ልጃገረዶች በአብዛኛዉ የአዋጊዎች የጭን ገረድ ናቸዉ።የወሲብ ባሪያ።« እግሬን ግጥም አድርገዉ በገመድ አሠሩት። እና ወሰዱኝ።ጫካ ከወሰዱኝ በኋላ ሁሉንም ከባድ ነገር ያሰሩናል።የአማፂያኑን ዕቃ አሸክመዉ እንድናጓጉዝ ያደርጉናል።ያንን ጌዜ ሳስበዉ ልቤ ይደማል።»ትላለች ኔሲፒዮ ታሻና።ስትታገት አሥራ-ስድት ዓመቷ ነበር።አምልጣ-ደቡብ ሱዳንዋ ከተማ ያመቢዮ የገባችዉ-ሁለት ራስዋን ነበር።

በደቡብ ሱዳንዋ የምዕራብ ኢኳቴሪያል ግዛት ዋና ከተማ ያምቢዮ ከአሸባሪዉ ቡድን ያመለጡ፤ ወይም የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ያስጣላቸዉ ታጋቾች የሚሰፍሩበት ጌዚያዊ ማዕከል አለ።ብዙዎቹ ሴቶች ወደ እዚሕ ሠፈር የሚመጡት ከአማፂያኑ ከወለዷቸዉ ልጆች ጋር ነዉ።

የመጠለያዉ ማዕከል ሐላፊ ጀስቲን ኢቤሬ እንደሚሉት አማፂዉ ቡድን በወንዶቹ ታጋቾች ላይ የሚፈፅመዉ በደልም ዘግናኝ ነዉ። አካላዊም-መንፈሳዊም።«ልጁ ወላጆቹን እንዲገድል ይታዘዛል።ልጁ ትዕዛዙን ሲፈፅም ወድሞቹ፤የአክስት አጎት ልጁቹ እና ሌሎች ዘመዶቹም እንዲያ ይገደዳሉ።ከዚያ በሕዋላ ገዳዩን ወላጆቹን ወይም ዘመዶቻችንን የገደለ እያሉ እረፍት ያሳጡታል።እሱም እነሱም የተሠራዉን አይረሱም።ሥለዚሕ ገዳዩ ከገዛ ዘመዶቹ ይገለላል።ዘምድናዉም ይሰበራል።»

የቡድኑ አባላት ቁጥር መቀነሱ ይነገራል።ግን ገና ክፉን-ደጉን ሳይለዩ በወላጅ-ዘመዶቻቸዉ ላይ ዘግናኝ ወንጀል ፈፅመዉ-ቡድኑን የተቀየጡት ወጣቶች የፈፀሙትንና የተፈፀመባቸዉን ግፍ ላለመቀጠላቸዉ ምንም ዋስትና የለም።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic