የዩክሬይን ውዝግብ እና ሩስያ ያቀረበችው ሀሳብ | ዓለም | DW | 08.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዩክሬይን ውዝግብ እና ሩስያ ያቀረበችው ሀሳብ

የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ትናንት በሞስኮ ከአውሮጳ የፀጥታ እና ትብብር ድርጅት ሊቀመንበር ዲድየ ቡርክሀልተር ጋ ስለ ዩክሬይን ውዝግብ ከመከሩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩስያ ቡድኖች

በዶንትሴክ እና በሉሀንስክ ግዛቶች የሚኖሩ ሦስት ሚልዮን የሩስያ ቋንቋ ተናጋሪዎች የፊታችን እሁድ እንዲያካሄዱት ያቀዱትን ውሳኔ ሕዝብ ወደሌላ ጊዜ እንዲገፉት፣ ከዚሁ ጎንም ምዕራቡ ዓለም ለዩክሬይን ውዝግብ መፍትሔ በሚያፈላልግ የወደፊት ድርድር ላይ በመንግሥቱ አንፃር የሚዋጉትን ሚሊሺያዎችንም እንዲያሳትፍ ሲጠይቁ ተሰምተዋል። የዩክሬይን ፕሬዚደንታዊ ምርጫም ፣ ከምርጫው በኋላ የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች መብት እስከተከበረ ድረስ እንደ አንድ ትክክለኛ ርምጃ ሊታይ እንደሚችል ጠቁመዋል። እርግጥ፣ ውሳኔ ሕዝቡን በተመለከተ ሩስያዊው ፕሬዚደንት ያቀረቡትን ሀሳብ የዩክሬይን የሽግግር መንግሥትም ሆነ መፍቀሬ ሩስያ ኃይላት አልተቀበሉትም።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic