የዩክሬይን ውዝግብ፣ ሩስያ እና ምዕራቡ ዓለም | ዓለም | DW | 29.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዩክሬይን ውዝግብ፣ ሩስያ እና ምዕራቡ ዓለም

ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ አካሂዳዋለች በሚሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ቀደም ሲል ጥለውት የነበረውን ማዕቀብ በትናንቱ ዕለት አጠናክረዋል። አዲሱ የዩኤስ አሜሪካ ማዕቀብ የተጣለው ለፕሬዚደንት

ለሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ቅርበት አላቸው በተባሉ ሰባት የሩስያ ባለሥልጣናት እና 17 ኩባንያዎች ላይ ነው። ማዕቀቡ በተጨማሪ ለሩስያ የጦር ኃይል አስፈላጊ የሆኑ ከውጭ የሚገቡ ከፍተኛ የቴክኒክ ቁሳቁሶችንም የሚመለከት ነው። ከአሜሪካውያኑ ጋ ሲነፃፀር የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ በግለሰቦች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው። ህብረቱ እንደ ዩኤስ አሜሪካ የሩስያን ኤኮኖሚ ወይም ፊናንስ ዘርፍ የሚነካ ጠንካራ ማዕቀብ እስከመጣል ግን ርቆ አልሄደም፣ ምክንያቱ ምን ይሆን? የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ቀደም ሲል ጠይቄው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic