የዩኤስ አሜሪካ የሬፑብሊካኖች ፓርቲ ጉባዔ | ዓለም | DW | 01.09.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዩኤስ አሜሪካ የሬፑብሊካኖች ፓርቲ ጉባዔ

የዩኤስ አሜሪካ ጠረፍን ባሰጋው ጉስታቭ በተባለው ከባህር በተነሳው ብርቱ አውሎ ነፋስ የተነሳ አራት ቀን የሚቆየው ይኸው ጉባዔ ለዛሬ ይዞት የነበረውን ብዙውን ፕሮግራም ጊዜው የፓርቲ ፖለቲካ ጊዜ አይደለም በሚል ምክንያት ሰርዞዋል

default

ማኬይንና ፔለን

የዩኤስ አሜሪካ የሬፑብሊካኖች ፓርቲ ሴኔተር ጆን ማኬንን እና ምክትላቸውን የአላስካ ሀገር አስተዳዳሪ ሴራ ፔሊንን የፊታችን ጥቅምት ወር መጨረሻ ለሚደረገው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዕጩ አድርጎ ለመሰየም ያዘጋጀውን ጉባዔ ዛሬ በይፋ ከፈተ።