የዩኤስ አሜሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብት ዘገባና ኢትዮጵያ | ዓለም | DW | 15.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዩኤስ አሜሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብት ዘገባና ኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ስላለው አስተያየት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እንዲያከብር ስለሚያደርገው ግፊት እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ ላይ ስለያዘው አቋም ዶቼ ቬለ ለአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር ላቀረበው ጥያቄ መሥሪያ ቤቱ መልስ ሰጥቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:37
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:37 ደቂቃ

የዩናይትድ ስቴትስ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብት ዘገባ


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሃገራትን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የቃኘበት ዓመታዊ ዘገባ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቀረቧል። ዘገባውን ያቀረቡት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር ጆን ኬሪ ሀገራቸውን ጨምሮ መንግሥታት በጥቅሉ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን እንዲያሻሽሉ ጠይቀዋል። ኬሪ በንግግራቸው አፍሪቃን አላነሱም። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ስላለው አስተያየት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እንዲያከብር ስለሚያደርገው ግፊት እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ ላይ ስለያዘው አቋም ዶቼ ቬለ ለአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር ላቀረበው ጥያቄ መሥሪያ ቤቱ መልስ ሰጥቷል። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘገቢያችን አጠናቅሮታል።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic