የዩኤስ አሜሪካ ምርጫ ውጤት እና አንደምታው | ዓለም | DW | 05.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዩኤስ አሜሪካ ምርጫ ውጤት እና አንደምታው

በዩኤስ አሜሪካ ትናንት በተካሄደው አጋማሽ የምክር ቤት ምርጫ ሬፓብሊካውያን በሁለቱም የምክር ቤት ክፍሎች አሸነፉ። በሕግ መምሪያው ምክር ቤት አብላጫውን ድምፅ የያዙት ሬፓብሊካውያን 100 መንበሮች ባሉት በሕግ መወሰኛው ምክር ቤትም ውስጥ 52 መንበሮችን በማግኘት አብላጫውን ድምፅ መያዝ ችለዋል።

የሬፓብሊካኖቹ ፓርቲ በምርጫዉ የተሳካ ውጤት ማግኘቱ የዴሞክራቱ ፓርቲያቸው የተሸነፈባቸው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በቀሩቸው ሁለት የሥልጣን ዓመታት በሚያንቀሳቅሱዋቸው ፖሊሲዎች እና በሚያነሱዋቸው አጀንዳዎች ላይ ወይም በፀደቁ ሕግጋት ላይ፣ ለምሳሌ፣ የጤና መዋቅራቸውን በመሰለው ሕግ ላይ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ይኖር ይሆን? ምንም እንኳን ሬፓብሊካኖቹ ባለፉት ዓመታትም ቢሆን ተባብረው ሲሰሩ ሳይሆን ሲያከላክሉ ቢታዩም። ስለ አሜሪካ ምርጫ አንደምታ የዋሽንግተኑን ወኪላችን አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic