የዩኤሱ ሴናት ምርጫና፣ የቃላት ጦርነቱ | የጋዜጦች አምድ | DW | 02.11.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የዩኤሱ ሴናት ምርጫና፣ የቃላት ጦርነቱ

ጥቂት ቀናት ለቀረዉ፣ ለዪናይትድ ስቴትሱ የምክር ቤት ምርጫ፣ እጩዎች የሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ተሟሙቆዋል

ቡሽ በምርጫዉ ቅስቀሳ ላይ

ቡሽ በምርጫዉ ቅስቀሳ ላይ

በአገሪቷ የሚገኙ ተንታኞች እና አዋቂዎች ለምርጫዉ እና ዉጤቱ የሚሰጡት ትንበያ ገና ከአሁኑ በፕሪዝደንት ቡሽ እና ከሁለት አመት በአሜሪካ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ተቀናቃኛቸዉ በነበሩት ጆን ኬሪ መካከል ጠንከር ያለ የቃላት ጦርነትን አስጀምሮአል።

በአሜሪካ የዲሞክራቶች ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ John Kerry እያደረጉ ያለዉ
የምርጫ ቅስቀሳ እና ቃላት አጠቃቀም ህዝቡ በዋይት ሃዉስ ላይ ያለዉ ጥርጣሪ ከፍ አድርጎታል። John Kerry በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በካሊፎርንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በተለይ ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባደረጉት ንግግር ላይ
«ትምህርታችሁን በትጋት እና በጥንካሪ ከሰራችሁ የቤት ሳራዎቻችሁንም በወቅቱ ካጠናቀቃችሁ ጥሩ ሊሆን ይችላል። አለበለዝያ ግን በኢራቅ ዉስጥ ተጣብቃችሁ ትቀራላችሁ።»

እንደ አ.አ 2004 ዓ.ም በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ እጩ የነበሩት ኬሪ በዚህ ንግግራቸዉ በቡሽ ላይ ማፊዝ እና፣ በቀልድ አሜሪካ በኢራቅ ትልቅ ሽንፈት እንደደረሰባት ነዉ መግለጽ የፈለጉት። የኬሪ ንግግር በቅስበት በአለም ከመሰራጨቱም በላይ የሪፓብሊካኑ ታዋቂ ፖለቲከኛ እና የቀድሞ ወታደር John McCain ኬሪ በአፋጣኝ እና በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ አዘዋል። የአሜሪካዉ ፕሪዝደት ጆርጅ ቡሽም ባለፈዉ ማክሰኞ በጆርጅያ ዉስጥ ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ፣
«የህዝብ እንደራሴዉ ኬሪ በጦር ግዳጅ ላይ ያሉትን ያልተማሩ ናቸዉ ማለታቸዉ ስድብ እና አስነዋሪ ነዉ። ከማሳቹሼትስ የመጡት እኝህ የህዝብ እንደራሴ ይቅርታ ሊጠይቋችሁ ይገባል። » ብለዋል። ኬሪ ስለዚሁ አነጋገራቸዉ ይቅታን መጠየቅ ወይም ማስተባበል አፈለጉም ።

«እኔን ማለት የቀድሞ ወታደር የነበርኩ የተናገርኩት ፣ ፕሪዝዳንት ቡሽን ሳይሆን በኢራቅ ያሉትን 140,000 ወታደሮች ነዉ ብሎ የሚያስብ ካለ፣ እብድ ነዉ።»

እንደ አሜርካዉያን፣ የቀድሞ የጦር አባላትን መስደብም ሆነ መተቸት አስነዋሪ ድርጊት ነዉ። ስለዚሁ ጉዳይ በአሜሪካ በተደረገዉ የመዘርዝር ጥያቄ እንደሚያሳየዉ ጆን ኬሪ በምርጫ ዘመቻ ቅስቀሳቸዉ ላይ ያደረጉት ንግግር በኢራቅ ያለዉን እዉነታ አስቀምጠዋል ሲል፣ ህዝቡ እወነታ እንዳላቸዉ አሳይቶአል።
የፖለቲካ ፓርቴዎችን ሁኔታ የሚያጠኑት Stuart Rothenberg የዲሞክራት ፓርቲ አራማጆቹ የምርጫዉን ዘመቻ ለማካሄድ አስተማማኝና ትልቅ ርእስ አግኝተዋል። ይኸዉም የፕሪዝደንት ቡሽ እና ስለኢራቅ የወቅቱ ሁኔታ ነዉ ባይ ናቸዉ።

በምርጫዉ ላይ የሚታየዉ የቃላት ጦርነት አስቂኝ ሲሆን በምርጫዉ ጆን ኬሪም ሆኑ ፕሪዝዳንት ቡሽ ለሚያራምዱት የፖለቲካ ፓርቲያቸዉ ለየት ያለ ድጋፍ እንዲሰጡ አልተጠየቁም። የፊታችን ማክሰኞ ጥቅምት 28 በሚደረገዉ ምርጫ ላይ ቡሽም ሆነ ጆን ኬሪ እንደማይገኙ ታዉቋል።

ጥቂት ቀናት ለቀረዉ፣ ለዪናይትድ ስቴትሱ የምክር ቤት ምርጫ፣ እጩዎች የሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ተሟሙቆዋል። በአገሪቷ የሚገኙ ተንታኞች እና አዋቂዎች ለምርጫዉ እና ዉጤቱ የሚሰጡት ትንበያ ገና ከአሁኑ በፕሪዝደንት ቡሽ እና ከሁለት አመት በአሜሪካ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ተቀናቃኛቸዉ በነበሩት ጆን ኬሪ መካከል ጠንከር ያለ የቃላት ጦርነትን አስጀምሮአል።

በአሜሪካ የዲሞክራቶች ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ John Kerry እያደረጉ ያለዉ የምረጡኝ ቅስቀሳ
እና ቃላት አጠቃቀም ህዝቡ በዋይት ሃዉስ ላይ ያለዉ ጥርጣሪ ከፍ አድርጎታል። John Kerry በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በካሊፎርንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በተለይ ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባደረጉት ንግግር ላይ