የዩኔስኮ ዓመታዊ ዘገባ | ኢትዮጵያ | DW | 29.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዩኔስኮ ዓመታዊ ዘገባ

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በምህፃሩ ዩኔስኮ የትምህርት ጥራት እየዘቀጠ መሄድ በዓለም ዙሪያ ከተጠበቀው በላይ መሃይምነት ይበልጥ እየተስፋፋ እንዲሄድ ማድረጉን አስታወቀ ።

ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባ እንዳስታወቀው ቁጥራቸው ወደ ሩብ ቢሊዮን የሚጠጋ ሕፃናት አንድን አረፍተ ነገር ጠንቅቀው ማንበብ አይችሉም ፤ ተገቢውን የሂሳብ ትምህርትም አያገኙም ። በአፍሪቃ በብዙ ሚሊዮን ለሚቀጠሩ ወጣቶች መሠረታዊ ትምህርት አለመዳረሱም አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ አዲስ አበባ ውስጥ አስታውቋል ። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ቢኖርም የጥራት ችግር እንዳልተወገደ ድርጅቱ አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic