የዩናይትድ ስቴት ጦር በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 17.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዩናይትድ ስቴት ጦር በአፍሪቃ

የሠፈረዉ ጦር ቁጥር መጨመርም ሆነ ወታደራዊ ሥልጠናዉና የጦር መሳሪያዉ መብዛት አፍሪቃ ዉስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችና የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል የፈየደዉ የለም የሚሉ አሉ።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን ለአፍሪቃ የሚሰጡት ወታደራዊ ድጋፍ ኢቦላን የመሳሰሉ ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል ሳይቀር ብዙ ጠቅሟል ባይ ናቸዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:52

የዩናይትድ ስቴት ጦር በአፍሪቃ

ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃ ዉስጥ ያሰፈረችዉ ጦር፤ ለአፍሪቃ ወታደሮች የምትሰጠዉ ሥልጠና እና የምታስታጥቀዉ ጦር መሳሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።የሠፈረዉ ጦር ቁጥር መጨመርም ሆነ ወታደራዊ ሥልጠናዉና የጦር መሳሪያዉ መብዛት አፍሪቃ ዉስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችና የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል የፈየደዉ የለም የሚሉ አሉ።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን ለአፍሪቃ የሚሰጡት ወታደራዊ ድጋፍ ኢቦላን የመሳሰሉ ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል ሳይቀር ብዙ ጠቅሟል ባይ ናቸዉ።ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃ ዉስጥ ከሁለት ሺሕ በላይ ወታደሮች አስፍራለች።የሰላዩ ቁጥር በግልፅ አይታወቅም።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ተከታዮን ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic