የዩናይትድ ስቴትስ ያየር ድብደባ | ዓለም | DW | 23.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የዩናይትድ ስቴትስ ያየር ድብደባ

ዩኤስ አሜሪካ በሶርያ የሚገኙ የ«አይ ኤስ» ሠፈሮች ትናንት ሌሊት ለመጀመሪያ ጊዜ በተዋጊ ጄቶች ማጥቃቷን የዩኤስ አሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር፣ ፔንታገን አስታወቀ።

ሩስያ ይህንኑ ሳውዲ ዐረቢያ፣ ቃታር፣ ዮርዳኖስ፣ ባህሬን እና የተባበሩት ዐረብ ኤሚሮች የተሳተፉበት ጥቃት የሶርያን የግዛት ሉዓላዊነት ያላከበረ እና ዓለም አቀፉን ሕግ የጣሰ ስትል ነቅፋለች።የ«አይ ኤስ» አማፂያኑ ደብዳቢዎችን ለመበቀል ዝተዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ «አሜሪካን የሚያሰጉ አሸባሪዎች» ያሏቸዉን ሐይላት ጦራቸዉ እገቡበት ገብቶ እንደሚያጠፋቸዉ ዛሬ በድጋሚ ዛቱ።ኦባማ፤ የአየርና የባሕር ሐይላቸዉ ሶሪያ ዉስጥ የሚገኙ ISIS እና አል-ኑስራ የተሰኙትን አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድናት ይዞታን ከደበደበ በኋላ ዛሬ እንዳሉት ድብደባዉ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።በድብደባዉ የሳዑዲ አረቢያ፤የዮርዳኖስ እና የሌሎች የሰወስት የአረብ ሐገራት የጦር ጄቶችም ተካፋዮች ነበሩ።አማፂያኑ ደብዳቢዎችን ለመበቀል ዝተዋል።ፕሬዝዳንት ኦባማ እንዳሉት ግን መንግሥታቸዉ ከሌሎች መንግሥታት ጋር በማበር የጀመረዉን ጥቃትይቀጥላል።የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic