የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅትና ጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 15.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅትና ጀርመን

ጀርመን ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጸጥታ መረጃ ልውውጥን በተመለከተ አዲስ ስምምነት ለማድረግ የምትሻ ሲሆን ፤ በዚህ ረገድ የወደፊቱ ግንኙነት ምን መሆን እንደሚገባው ፤ የህዝብ እንደራሴዎቿን ም/ቤት ዛሬ አከራክሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀጥታ ድርጅት ከሀገር ውጭ በዓለም ዙሪያ፣ በተለያዩ አገሮች፣ 100,000 ያህል ኮምፒዩተሮችን ለስለላ በመትከል ፣ መረጃ መሰብሰብ መቻሉን ኒውዮርክ ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ በትናንቱ እትሙ መግለጹ የሚታወስ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ጀርመን ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጸጥታ መረጃ ልውውጥን በተመለከተ አዲስ ስምምነት ለማድረግ የምትሻ ሲሆን ፤ በዚህ ረገድ የወደፊቱ ግንኙነት ምን መሆን እንደሚገባው ፤ የህዝብ እንደራሴዎቿን ም/ቤት ዛሬ አከራክሯል።
የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤልን ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮታል።

አበበ ፈለቀ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic