የዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ መብት ዘገባና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 01.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ መብት ዘገባና ኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዘገባ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ችግር እያለ ከጠቀሳቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል በዋነኝነት ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣለው ገደብ፣ ፖለቲካዊ መነሻ ያላቸው የፍርድ ሂደቶች፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀም ወከባና ማሸማቀቅ ይገኙበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:54 ደቂቃ

የዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ መብት ዘገባና ኢትዮጵያ


በጎሮጎሮሳዊው 2014 ዓም በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ችግሮች ደርሰዋል ሲል የዩናይትድ ስቴትስ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ዘገባ አስታወቋል። ይኽው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዘገባ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ችግር እያለ ከጠቀሳቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል በዋነኝነት ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣለው ገደብ፣ ፖለቲካዊ መነሻ ያላቸው የፍርድ ሂደቶች፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀም ወከባና ማሸማቀቅ ይገኙበታል። ዘገባው በሲቪክ ማህበራትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የተጣለው ገደብ መቀጠሉንም አስታውሷል። በሀገሪቱ በዘፈቀደ ግድያ እንደሚካሄድና ሰዎችም ክስ ሳይመሰረትባቸው እንደሚታሰሩና እንደሚደበደቡና ቁም ስቅል እንዲያዩ እንደሚደረግ በዘገባው ተጠቅሷል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዘገባ አለው ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic