የዩናይትድ ስቴትስ ዉንጀላና ኢራን | ዓለም | DW | 12.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የዩናይትድ ስቴትስ ዉንጀላና ኢራን

የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የኢራን መንግሥት አካላት ሴራዉን በበላይነት ሲመሩና ሲያቀነባብሩ ነበር።የኢራን ባለሥልጣናት ግን የዩናይትድ ስቴትስን ዉንጀላ «የሕፃናት ጨዋታ» ና «የሙያ ቢሶች» ክስ በማለት አጣጥለዉ ነቅፈዉታል

default

በዋሽንግተን-የሳዑዲ አረቢያዉ አምባሳደር

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በዋሽንግተን የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደርን ለመግደል ኢራን «የሸበረችዉ» ያሉትን ሴራ ማክሸፋቸዉን ትናንት አስታዉቀዋል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የኢራን መንግሥት አካላት ሴራዉን በበላይነት ሲመሩና ሲያቀነባብሩ ነበር።የኢራን ባለሥልጣናት ግን የዩናይትድ ስቴትስን ዉንጀላ «የሕፃናት ጨዋታ» ና «የሙያ ቢሶች» ክስ በማለት አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።የኢራን መንግሥት እንደሚለዉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በዚሕ ወቅት ኢራንን የወነጀሉት የአሜሪካን ምጣኔ ሐብታዊ ሥርዓት በመቃወም አደባባይ የሚወጣዉን አሜሪካዊ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ነዉ።ባአሜሪካኖች ክስ ላይ ያተኮረዉን ዘገባ የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic