የዩናይትድ ስቴትስ መርህና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 03.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ መርህና ኢትዮጵያ

ከሳምንታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምክትልነት የተሰየሙት ዌንዲ ሻርማን ኢትዮጵያን ለአጭር ቀናት ጎብኝተዉ ነበር።

አሜሪካዊቱ ፖለቲከኛ ዌንዲ ሻርማን በዚህ ወቅት የሀገሪቱን አስተዳደርና የምርጫ ይዞታ አስመልክተዉ የሰነዘሩት አስተያየት በራሳቸዉ ላይ ትችት ከማስከተሉ ባሻገር የሚሠሩበት መሥሪያ ቤት የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስቴር በየዓመቱ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ አስመልክቶ ከሚያወጣዉ ዘገባ የሚጣረስ መሆኑ ግርምትና ጥያቄዎችን አስከትሏል። ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮም ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾችና ገለልተኛ አጥኚዎች ትችታት ተቃዉሟቸዉን በይፋ አሰምተዋል። ትችትና ተቃዉሞዉም ለመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ወይም መርህ ምንድነዉ? ተለዉጧልስ ወይ የሚል ጥያቄን ያዘለ ነዉ። ዶይቼ ቬለም የዚህ ሳምንት የእንወያይ ርዕሱ አድርጎታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic