የዩኒቨርሲት መግብያ ነጥብ ይፋ ሆነ | ይዘት | DW | 26.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ይዘት

የዩኒቨርሲት መግብያ ነጥብ ይፋ ሆነ

በትምህርት ሚንስቴር የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጄንስ በትላንትናዉ እለት የ2009 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲት መግቢያ ዉጤትን ይፋ ማድረጉ የአገር ዉስጥ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:22

ዩኒቨርሲት መግብያ ነጥብ

ተፈታኞች በአገረቱ ዉስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት ስለነበረና ፈተናዎቹ ሾልከው ኢንቴርኔት ላይ ስለወጡ ፈተናዉን መፈተን በጣም አሳስቧቸዉ እንደነበር ስንዘግብ ነበር።


አጄንስዉ ባወጣዉ መግለጫ ለ2009 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛና የማታ ተማርዎች ለወንዶች 354 እና ለሴቶች 340 ስሆን፣ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንዶች 330 ስሆን ለሴቶች ደግሞ 320 መሆኑን ማግለጫዉ ጠቅሰዋል።


ፈተናዉን የተፈተኑት ተማርዎች ከፈተናው በፊት የተፈጠሩት ችግሮች በዉጤታችሁ ላይ ምን ጫና አሳድሮባችኋል ብለን ጠይቀን ነበር። በደቡብ ዋሎ የደሴ ነዋር መሆናቸውን የጠቀሱት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማር «እኔ 420 ናዉ ያመጣሁት» ይላሉ። ለዝህም ደስተኛ መሆናቸዉን ከተናገሩ በዋላ ዉጤቱን በተመለከተ «እኔን ብቻ ሳይሆን ባአገርቱ የምፈተኑትን ማየት አለብን» ይላሉ።


አሁን ኢየተወራ ያለዉ ስለ ነጥቡ ብቻ ሳይሆን የአገርቱን ሰላም በተመለከተ ተማርዉ ወደ ዩኒቨርስት ገቢቶስ ምን ተሳፋ አለዉ የምል ነዉ ይላሉ።

አቶ እንዳልካቸዉ መኮኒን የተባሉ የአድስ አበባ ነዋር የሆኑት፣ የግል ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የህሳብ መምህር መሆናቸዉን ተናግሮ በግል ትምህርትቤቶች በአማካይ ከፍተኛ ነጥብ እንደምታይ ግን «ክፍለ አገር ላይ ከነበረዉ ጫና አኳያ ዉጤቱ ኢሄን ያህል ላይሆን ይችላል» ይላሉ።


የአዳማ አከባብ ነዋር የሆኑት በአካባያቸዉ ያሉት ተማርዎች በነበረዉ ተቃዉሞ ብዙም ስላልተዘጋጁበት ፈተናዉን መፈተን ጭቅጭቅ ፈጥሮ እንደነበር፣ በዛ ላይ ተዳሚሮ የነጥቡ ከፍ መደረጉ እንዳኮረፋቸዉ ይናገራሉ።

የትምህርት ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ተክሌ በኦሮሚያ የነበረዉ አለመረጋጋትና ፈተና ሾልኮ መዉጣቱ የተማርዎች ስነልቦና ላይ ተፅኖ እንደምኖረዉ ተናግሮ ስለ ዩኒቨርስት መግቢያ ነጥብ የዩኒቨርስት የመቀበል አቅም ላይ ተመስርቶ ነዉ።

የማለፊያ ውጤቱ ከፍ ማለቱን የጠቀሱ የፌስቡክ ድረ ገፃችን ተጠቃሚዎች እንዳሉት፣ ተረጋግተው ፈተናዉን ባለመፈተናቸው፣ ያመጡትን ውጤት አመርቂ አይደለም።

መርጋ ዮናስ

አሪያም ተክሌ

Audios and videos on the topic