የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዝቅተኛው ነጥብ ይፋ ተደረገ | ኢትዮጵያ | DW | 11.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዝቅተኛው ነጥብ ይፋ ተደረገ

የሳይንስን እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚንሥቴር ለ2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዝቅተኛው ነጥብ 140 እንዲኾነ ይፋ አደረገ። ሚንሥቴር መሥሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ የፈተና ዉጤት «የጋሽበባቸዉ» ያላቸዉን 5 የትምሕርት ዓይነቶች ዉጤት ዉቅድ አድርጓል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:55

ዝቅተኛው ነጥብ 140 እንዲኾነ ይፋ ተደረገ

የሳይንስን እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚንሥቴር ለ2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዝቅተኛው ነጥብ 140 እንዲኾነ ይፋ አደረገ። ሚንሥቴር መሥሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ የፈተና ዉጤት «የጋሽበባቸዉ» ያላቸዉን 5 የትምሕርት ዓይነቶች ዉጤት ዉቅድ አድርጓል።  ዘንድሮ አወዛጋቢዉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተፈተኑት ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 73 በመቶ ማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውም ተገልጧል። ቀደም ሲል የዘንድሮ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ በተለያዩ አካላት ቅሬታ አስነስቶ ነበር። በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተመሳሳይ ከፍተኛ ነጥብ ሌሎች ቦታዎች ደግሞ ዝቅተኛ  ነጥብ እንዲመዘገብ ሰበብ ፈጥሯል የተባለው ስህተት ካልታረመ ርምጃ ለመውሰድ የዛቱ አካላትም ነበሩ። በአራት የትምህርት አይነት ከ400 አጠቃላይ ነጥብ ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ መቁረጥ ለምን እንዳስፈለገ ሚንሥቴር መሥሪያ ቤቱ አብራርቷል። 

ሚኒስቴሩ እንደሚለዉ የዘንድሮዉ ፈተና ዉጤት የሚበየነዉ በአራት የትምህርት ዓይነቶች ከ400  ብቻ ነዉ። አራቱ የትምህርት ዓይነቶች፤ ለተፈጠሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦ በእንግሊዝኛ፣ በሒሳብ፣ በስኮላስቲክ አፕቲትዩድ እና በፊዚክስ ሲሆኑ፤ የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ፦በእንግሊዝኛ፣ በሒሳብ፣ በስኮላስቲክ አፕቲትዩድ እና በጂኦግራፊ ያመጡት ዉጤት ብቻ ይያዛል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች