የየመን ፖለቲካዊ ቀዉስና ድርድር | ዓለም | DW | 03.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የየመን ፖለቲካዊ ቀዉስና ድርድር

ርዕሠ-ከተማ ሠነዓን ጨምሮ አብዛኛ ሐገሪቱን የሚቆጣጠሩት የሁቲ አማፂያን፤ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረቱ የሠጡት የሠወስት ቀን ቀነ-ገደብ ነገ ማምሻዉን ያበቃል።

የየመን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሸምጋይነት የሚያደርጉት ድርድር እስካሁን ለአግባቢ ዉጤት አልበቃም። ርዕሠ-ከተማ ሠነዓን ጨምሮ አብዛኛ ሐገሪቱን የሚቆጣጠሩት የሁቲ አማፂያን፤ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረቱ የሠጡት የሠወስት ቀን ቀነ-ገደብ ነገ ማምሻዉን ያበቃል።ፖለቲከኞቹ እስከ ነገ-ድረስ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት ካልተግባቡ ሐገሪቱን እንደሚገዙ አማፂያኑ አስጠንቅቀዋል።የሠነዓዉ ተባባሪ ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት እንደሚለዉ የየመን ፖለቲከኞች የሽሽግር መንግሥት ካልመሠረቱ ወይም አማፂያኑ ቀነ ገደቡን ካላራዘሙ ሐገሪቱ ከባሰ ትርምስ መግባቷ አይቀርም።

ግሩም ተክለ ኃይማኖት

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic