የየመን ፕሬዝዳት ያደረጉት ሹም ሽር | ዓለም | DW | 12.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የየመን ፕሬዝዳት ያደረጉት ሹም ሽር

ፕሬዝዳቱ ሐዲ ሪፐብሊካን ጋርድ የተሰኘዉን ጠንካራ ክፍለ-ጦር የሚያዙትን የሳሌሕን ልጅ ጄኔራል አሕመድ ዓሊ ሳሌሕን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የየመን አምባሳደር፥ የቀድሞዉን ፕሬዝዳት ሁለት የቅርብ ዘመዶችን ደግሞ በኢትዮጵያና በጀርመን የየመን ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ አድርገዉ ከአጠገባቸዉ አርቀዋቸዋል

A general view shows the Yemeni capital Sanaa's Old City on January 15, 2010. An air strike on an Al-Qaeda in the Arabian Peninsula (AQAP) position in north Yemen killed six suspected leaders of the group including its military boss, a senior Yemeni official said. The military chief, Qassem al-Rimi, was among 23 people who made a daring escape from a state security prison in Sanaa in February 2006 that left the government red-faced. AFP PHOTO/AHMAD GHARABLI (Photo credit should read AHMAD GHARABLI/AFP/Getty Images)

ሠነዓ-በከፊል

የየመን ፕሬዝዳት አብድ ረቡ መንሱር ሐዲ ጠንካራ ተቀናቃኞቻቸዉ የሚባሉት የቀድሞዉን ፕሬዝዳት የዓሊ አብደላ ሳሌሕን ልጅና የቅርብ ዘመዶች ከየጦር አዛዥነት ሹመታቸዉ ሽረዉ በአምባሳደርና በወታደራዊ አማካሪነት ሾመዋቸዋል። ፕሬዝዳቱ ሐዲ ሪፐብሊካን ጋርድ የተሰኘዉን ጠንካራ ክፍለ-ጦር የሚያዙትን የሳሌሕን ልጅ ጄኔራል አሕመድ ዓሊ ሳሌሕን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የየመን አምባሳደር፥ የቀድሞዉን ፕሬዝዳት ሁለት የቅርብ ዘመዶችን ደግሞ በኢትዮጵያና በጀርመን የየመን ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ አድርገዉ ከአጠገባቸዉ አርቀዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ የቀድሞዉን ፕሬዝዳት ዋነኛ ተቀናቃኝ ጄኔራል ዓሊ ሞሕሴንን ባንፃሩ ልዩ አማካሪያቸዉ አድገዉ ሾመዋቸዋል። እርምጃዉ ፕሬዝዳት ሐዲ አስጊ ተቀናቃኞቻቸዉን አርቀዉ ከአንድ ዓመት በፊት የያዙትን ሥልጣን ለማጠናከር የተጠቀሙበት ሥልት መሆኑ በግልፅ እየተነገረ ነዉ። ሰነዓ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለ ሐይማኖትን ሥለ ሹም ሽሩ አላማና እንድምታ በሥልክ አነጋግሬዋለሁ። ለመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ከሰጠዉ መልስ ይጀምራል።

ግሩም ተክለ ሐይማኖት

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic