የየመን ዉዝግብና የዓረቡ ዓለም | አፍሪቃ | DW | 27.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የየመን ዉዝግብና የዓረቡ ዓለም

ሳውዲ ዓረቢያ ግብፅ ሱዳን ጨምሮ አስር ሀገራት የየመን ፕሬዚደንት አቤድ ራቦ ማንሱር ሀዲን በመፃረር የሚዋጉትን የሁቲ ዓማፅያን ማጥቃት ከጀመሩ አንድ ቀን አልፏል።


የሳውዲ ዓረቢያ የጦር አዉሮፕላኖች የሁቲ አማፅያን ኃይሎች የያዟቸዉን አካባቢዎች ደብድበዋል። በየመን ጦር እና በዐይን እማኞች ዘገባ መሠረት፣ ጥቃት የጀመሩት የሳውዲ ተዋጊ ጄቶች ዒላማ ያደረጉት በመዲናይቱ ሰንዓ በሚገኙት የሁቲ ሚሊሺያዎች ሠፈሮችን ነው። በየመን ውዝግብ ጣልቃ የገቡት የዉጭ ኃይሎች ወደሳዉድ አረብያ የሸሹት የየመኑ ፕሬዚደንት ከጥቂት ቀናት በፊት ያቀረቡትን የርዳታ ጥሪ በመቀበል መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ። ኢራን በበኩልዋ የሳዉድ አረብያ በየመን ጣልቃ መግባትዋ ታላቅ መዘዝ ይኖረዋል ስትል አስጠንቅቃለች። የወቅቱ የየመን ጥቃት ሳዉድ አረብያንና ኢራንን ከእጅ አዙር ጦርነት ወደግልፅ ወደ ግጭት ያስገባ ይሆን? የሳዉዲ የብዙኃን መገናኛዎች ስለየመኑ ዉዝግብና ጦርነት ምን ይላሉ? ጅዳ ሳዉዲ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን እዚህ አነጋግረነዉ ነበር።

ነብዩ ሲራክ

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic