የየመን ተቀናቃኝ ሐይላት ዉጊያ | ዓለም | DW | 23.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የየመን ተቀናቃኝ ሐይላት ዉጊያ

ከፊል ሰነዓን ባመሰቃቀለዉ ዉጊያ 350 ሐምሳ ያክል ሰዎች ተገድለዋል።በሺሕ የሚቆጠሩትን ከቤት ንብረታቸዉ አፈነቃሏል።ሁለቱ አማፂያንና የሐገሪቱ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሸምጋይነት ተኩስ ለማቆም ከተስማሙ ካለፈዉ ዕሁድ ወዲሕ ግን ከተማይቱ ተረጋግታለች።

የየመን ተቀናቃኝ አማፂ ሐይላት በሐገሪቱ ርዕሠ-ከተማ ሰነዓ ዉስጥ የገጠሙት ዉጊያ ሠሞኑን ጋብ ብሏል።በመንግሥት ጦር እና ሁቲ በተባሉት የሺዓ አማፂያን መካከል ይደረግ የነበረዉ ዉጊያ ርዕሠ-ከተማይቱ ሲደረስ ከመንግሥት ያፈነገጡ አንድ ጄኔራል በሚመሩት ጦርና በሁቲ አማፂያን መካከል ቀጥሎ ነበር።ከፊል ሰነዓን ባመሰቃቀለዉ ዉጊያ 350 ሐምሳ ያክል ሰዎች ተገድለዋል።በሺሕ የሚቆጠሩትን ከቤት ንብረታቸዉ አፈነቃሏል።ሁለቱ አማፂያንና የሐገሪቱ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሸምጋይነት ተኩስ ለማቆም ከተስማሙ ካለፈዉ ዕሁድ ወዲሕ ግን ከተማይቱ ተረጋግታለች።የሰነዓ ተባባሪ ወኪላችን ግሩም ተክለ ሐይማኖትን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ግሩም ተክለሐይማኖት

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic