የየመን ቀውስ እና የለጋሾች ጉባኤ  | ዓለም | DW | 27.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የየመን ቀውስ እና የለጋሾች ጉባኤ 

በአሁኑ ጊዜ በየመን በረሀብ ለተጎዱት ከሚያስፈልገው እርዳታ በተጨማሪ እርዳታውን ለተጎጂዎች እንዴት ማድረስ ይቻላል የሚለውም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:39

የየመን ቀውስ እና የለጋሾች ጉባኤ 

የርስ በርስ ጦርነት በሚካሄድባት በየመን በገባው ረሀብ ለተጎዱት መርጃ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ  ከትናንት በስተያ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ በተካሄደው የለጋሽ ሀገራት ጉባኤ ላይ ከሚያስፈልገው ገንዘብ ግማሽ ያህል ቃል ተገብቷል ። ጉባኤውን የመሩት የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬስ  ድርጅቱ በዚህ ዓመት ለየመን ያስፈልጋል ያለውን ገንዘብ በሙሉ የሚያገኝ ባይሆንም ግማሹንም ቢሆን ለመስጠት ቃል የገቡትን አወድሰዋል ። በአሁኑ ጊዜ በየመን በረሀብ ለተጎዱት ከሚያስፈልገው እርዳታ በተጨማሪ እርዳታውን ለተጎጂዎች እንዴት ማድረስ ይቻላል የሚለውም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ።ስለ እርዳታ አሰባሰቡ እና በየመን ለበረሀብ ለተጎዱት እርዳታ ለማድረሱ በሚያጋጥመው ችግር ላይ የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 
 

Audios and videos on the topic