የየመን ቀውስ ተባብሷል | ዓለም | DW | 03.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የየመን ቀውስ ተባብሷል

የመን ቀውስ ውስጥ ከገባች አምስትኛ ወሯን ልታገባድድ ነው። ፕሬዝዳንት አንደላ ሳሌህ ስልጣን ለመልቀቅ የጀመሩትን ስምምነት አልፈርምም አሉ።

default

ፕሬዝዳንት አብደላህ ሳሌህ የ32 ዓመት ቆይታቸው እንዲያበቃ በመጠየቅ አደባባዩን፤ ጎዳናውን አጨናንቀው የከረሙት የመናውያን ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን ካልወረዱ ትግላችን አይቆምም ብለው በአቋማቸው እንደጸኑ አሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ እስከአሁን ተገድለዋል። ፕሬዝዳንት ሳሌህ በኳታር መሪነት በተጀመረው ሽምግልና ስልጣናቸውን በአንድ ወር ውስጥ እንደሚለቁ፤ ለዚህም በወንጀል እንዳይጠየቁ ይደረግ ዘንድ ተስማምተው ነበር። ይሁንና ሊያስፈርሟቸው ለመጡት የሸምጋይ ቡድን አባላት እምቢኝ ብለው ስምምነታቸውን ማፍረሳቸው ከሰሞኑ ተሰምቷል። የመናውያን ግን ተቃውሞአቸውን እንደቀጠሉ ናቸው። ትላንትናና ከትላንት በስቲያ በተለያዩ የየመን ከተሞች ተቃውሞው ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የተከታዩ የነቢዩ ሲራክ ዘገባ የሚያሳየው።

ነቢዩ ሲራክ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic