የዞን ዘጠኝ ፀሃፊዎች ለማርቲን ኤናልስ ሽልማት መመረጣቸው | ኢትዮጵያ | DW | 27.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዞን ዘጠኝ ፀሃፊዎች ለማርቲን ኤናልስ ሽልማት መመረጣቸው

ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለአንድ ዓመት ከ6 ወር ታስረው የተፈቱት «ዞን ዘጠኝ» የተሰኘዉ አምደ መረብ ፀሃፍት ኢትዮጲያ ዉስጥ ይፈፀማል ስለሚባለው የሰዉ መብት ጥሰት ባቀረቡት ፁሁፍ በሽብር ወንጀል ተከሰው መታሰራቸው ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

የዞን ዘጠኝ ፀሃፊዎች

መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተከሰሱት እነዚሁ ፀሃፍት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ከእስር ተፈተዋል። ከእስር ይፈቱ እንጅ ከሃገር እንዳይወጡ መንግስት የጎዞ ሰነዶቻቸው እንደተቀበላቸዉ እና አሁንም ማስፈራሪያዎች እንደምደርስባቸዉ ተናግረዋል።

ስራቸዉን በተመለከተ የአለም ዓቀፍ የፕሬስ ነፃነት እና የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ሽልማት እንዳገኙ ዘገባዎች ያሳያሉ። ዛሬ ደግሞ ለስዊዘርላንዱ የማርቲን ኤናልስ መታሰቢያ ሽልማት ተመርጠዋል ። የማርትን ኤናልስ ሽልማት ስራ አስከያጅ ሚካኤል ካምባታ ሽልማቱ የሚሰጠው በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ለሚሟገቱ መሆኑን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። በ 10 ዳኞች ዞን ዘጠኝን ጨምሮ ለሽልማቱ የቻይና እና የሶርያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችም ተመርጠዋል ።

የዞን 9 ፀሀፍት እንዴት ለሽልማቱ እንደተመረጡ ካምባታ ሲናገሩ፣ <<እኔ የማስበዉ ዳኞቹ ጸሀፍቱን የመረጡበት ምክንያት ጸሃፊዎቹ ቴክኖሎጅዉ ያመጣውን አዲስ ፈጠራ መጠቀማቸዉ ነዉ። ጸሃፍቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ እና እትዮጲያ ዉስጥ ያለዉን የእስረኞች ሁኔታ ለማጋለጥ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ለመጠቀም ሞክረዋል። ይህም የደዳኞቹን ቀልብ ስቧል። በተጨማሪም ፀሃፍቱ የተጋፈጧቸው ችግሮችም አሉ ፣ አሁንም ከአንድ ሰዉ በስተቀር አምስቱም እንዳይጓዙ ገደብ ተጥሎባቸዋል፣ በፊትም ሃሳባቸውን በነፃ ስለገለፁ ብቻ በሽብር እና በሌሎችም ወንጀሎች ተከሰዋል ። ዳኞቹም እንደዚህ ያሉትን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በዚህ ሽልማት እና በስራቸው ጥበቃ ለመስጠት ስለሚፈልግ ነዉ።>>


ከሦስቱ አንደኛ የሚሆነው ተሸላሚ በመጭዉ ጥቅምት እንደሚታወቅ የሚናገሩት ካምባታ አንደኛ አሸናፍ ወይም ሎሬት ተብሎ የምጠራዉ 20,000 የስዊስ ፍራንክ፣ ሁለተኛዉ እና ሶስተኛዉ ደግሞ 5000 የስዊስ ፍራንክ እንደሚያገኙ እና ሶስቱም እያንዳንዳቸው ሰብዓዊ መብት ጥበቃ የሚያውሉት 11, 650 የስዊስ ፍራንክ ከጀኔቫ የከተማ አስተዳደር እንደሚሰጣቸው ካምባታ ተናግረዋል።

እትዮጲያ የሰብዓዊ መብት ከሚጥሱ አገራት ተርታ እንዳለች የሚጠቅሰዉ ከፀሃፍቱ አንዱ በፍቃዱ ሃይሉ ሽልማቱ ይገባናል ብሏል። የመመረጣቸው ዜና ሲሰማ ደስ እንዳለዉ የተናገረው ሌላኛዉ የዞን ዘጠኝ ፀሃፊ ዘላለም ክብረት ለሽልማቱ መመረጣቸው ትልቅ ትርጉም እንዳለዉ እና ወደፊትም የይበልጥ በሰብዓዊ መብት ላይ ለመስራት ማቀዳቸዉን ይናገራል።

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic