የዝምባብዌ የትምህርት ደረጃ ማሽቆልቆልና የአርክቲክ ይዞታ ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 04.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የዝምባብዌ የትምህርት ደረጃ ማሽቆልቆልና የአርክቲክ ይዞታ ፣

የደቡባዊው አፍሪቃ የዳቦ ቅርጭት የነበረችው ሀገር ዝምባብዌ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ለረሃብና ኮሌራ መጋለጧ እሙን ነው። ዝምባብዌ፣ የውጭ ተጽእኖ አላጋጠማትም ባይባልም፣ ለደረሰባት ብርቱ ቀውስ፣ ኀላፊዋ ራሷ ፣ በይበልጥም የፖለቲካ መሪዎቿ ናቸው።

default

በምድር ሙቀት ጭማሪ ሳቢያ፣ የበረዶ ክምር በመሟሟት ላይ የሚገኝበት፣ አርክቲክ፣

ከዝምባብዌ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች አንዱ ትምህርት ነው። በትምህርት ይዞታ፣ በሥርዓተ-ትምህርት ከአፍሪቃ አንደኛ እንደነበረች የሚነገርላት ዝምባብዌ፣ አሁን ፣ አሁን ደረጃዋ ክፉኛ ማሽቆልቆሉ ነው የሚታወቀው።

በቅርቡ፣ የአርክቲክ ውቅያኖስ አዋሳኝ አገሮች፣ በትሮምሶ፣ ኖርዌይ በመሰብሰብ ፣ የአካባቢው ጥሬ ሀብት፣ በሚመጡት 50 ዓመታት እንዳይነካ ይታወጅ ዘንድ፣ በጉባዔው ጥሪ አቅርበዋል።

TY,NM