የዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ | ኢትዮጵያ | DW | 08.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ

የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ‘ በሚል ርዕስበተካሄደ ውይይት ላይ የተካፈሉ ተሳታፊዎች ሴቶች መብታቸውን ለማስከበርም ሆነ በአገራቸው ተጠቃሚ ለመሆን በየመስኩ ተሳትፎአቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

Äthiopien - Wahlen / Frau bei Stimmabgabe

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ እንዳይል የሚገድቡ እንቅፋቶችን ማስወገድ እንደሚገባ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ውይይት ላይ ተገለፀ ።Vision Ethiopian Congress for Democracy የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ‘የዜጎች በተለይም የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ‘ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ውይይት ላይ የተካፈሉ ተሳታፊዎች ሴቶች መብታቸውን ለማስከበርም ሆነ በአገራቸው ተጠቃሚ ለመሆን በየመስኩ ተሳትፎአቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ። በአጠቃላይ በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኤኮኖሚም ሆነ በማህበራዊ ጉዳዮች በንቃት የሚሳተፉ መብታቸውን የሚጠይቁ ና የሚያስከብር ዜጎች ማፍራት እንደሚገባ የድርጅቱ ሃላፊ ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት አስታውቀዋል ። ዝርዝሩ ከአዲስ አበባ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic