ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ፤ ሌላ ሳምንት። ሌላ ጭፍጨፋ። ተመሳሳይ ሥፍራ፣ ተጨማሪ ሐዘን፣ ቁጣና ዉግዘት።ወለጋ-የደም አምባ።የትናንቱ ቄሌም ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ፣ መንደር 20ና 21 ዉስጥ ነዉ። ከጭፍጨፋዉ ያመለጡ ነዋሪዎች እንደሚሉት በጥቃቱ ከ170 እስከ 300 የሚደርሱ በአብዛኛዉ የአማራ ተወላጆች በመደዳ ተገድለዋል።
ዩክሬይን እህል ከሃገሬ ዘርፎ ወጥቶአል ያለችዉን የሩስያን መርከብ ጥቁር ባህር ዳርቻ ላይ ይዛ እየመረመረች እንደሆን ቱርክ ዛሬ ዐስታወቀች። በቱርክ የዩክሬይን አምባሳደር እንደተናገሩት «ዚቢክ ዞሊ» የተባለዉ እና የሩስያን ባንዲራ ያነገበዉ ግዙፉ የሩስያ የጭነት መርከብ፤ በቱርክ የጉምሩክ ባለሥልጣን ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ገብቶአል።
ሩሲያ በዩክሬይን ላይ ጦርነት ከጀመረች ከአራት ወራት ገደማ በኋላ ከአርባ አገሮች የተውጣጡ ልዑካን በሉጋኖ ስዊዘርላንድ ሀገሪቱን መልሶ በመገንባት ላይ መወያየት ጀመሩ። በጦርነት የተመታችዉ ሃገር የዩክሬይን መንግስት ለመልሶ ግንባታው ሂደት ቅድሚያ መስጠት የሚፈልጋቸዉን ነገሮች በስዊዘርላንድ በሚካሄደዉ ዉይይት ላይ ማቅረብ እንደሚፈልግ ተነግሮአል።
የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ኤኮዋስ) በማሊ እና በቡርኪናፋሶ ላይ ያሳረፈዉን የኤኮኖሚ እና የገንዘብ ማዕቀብ አነሳ። ኤኮዋስ ዉሳኔዉን ያሳለፈዉ የሁለቱ ሃገራት ወታደራዊ መሪዎች በየሃገራቸዉ በ 24 ወራት ጊዜ ዉስጥ ምርጫ አካሄደዉ የዴሞክራሲ ሽግግር እንደሚያደርጉ ካሳወቁና አዲስ የምርጫ ሕግ በጽሑፍ ለማኅበሩ ካቀረቡ በኋላ ነዉ።