የዛምቢያ ፕሬዚደንት ሥርዓተ ቀብር | አፍሪቃ | DW | 11.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዛምቢያ ፕሬዚደንት ሥርዓተ ቀብር

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዛምቢያ ፕሬዚደንት ማይክል ሳታ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመዲናይቱ ሉሳካ ተፈፀመ። የፕሬዚደንት ሳታ ይፋ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከ50,000 የሚበልጡ የሀገሪቱ ዜጎች እና በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በአርበኞች ስቴድየም ውስጥ ነበር የተከናወነው።

በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከተሳተፉት መሪዎች መካከል የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚደንት ኬኔት ካውንዳ፣ የዚምባብዌ እና የኬንያ ፕሬዚደንቶች ሮበርት ሙጋቤ እና ኡሁሩ ኬንያታ ሲጠቀሱ ፣ የናሚቢያ እና የማዳጋስካር ጠቅላይ ሚንስትሮች እና በርካታ ምክትል ፕሬዚደንቶችም ተገኝተዋል። በዛሬው የቀብር ሥነ ሥርዓት ምክንያት በዛምቢያ ትምህርት ቤቶች፣ መደብሮች እና የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ተዘግተው ውለዋል።

ዛምቢያን እአአ ከ2011 ዓም ወዲህ የመሩት የ77 ፕሬዚደንት ማይክል ሳታ እአአ ባለፈው ጥቅምት 28 ነበር ከረጅም ህመም በኋላ ህክምና ያደርጉባት በነበረችው የብሪታንያ መዲና ለንደን ሕይወታቸው ያለፈችው። በዛምቢያ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ አዲስ ፕሬዚደንት እስኪመረጥ ድረስ ትውልደ ስኮትላንድ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንት ጊ ስኮት ሀገሪቱን ይመራሉ።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ