የዚምባቡዌ ፖለቲካዊ ቀዉስ | አፍሪቃ | DW | 16.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

 የዚምባቡዌ ፖለቲካዊ ቀዉስ

የዚምባብዌ ጦር የሐገሪቱን የረጅም ጊዜ መሪ ሮበርት ሙጋቤን ከሥልጣን በማስገዱ ሰበብ የተፈጠረዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ ይወገድ ዘንድ የተለያዩ መንግሥታት እና ማሕበራት እየጠየቁ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:20

 ዚምባቡዌ

የዚምባቡዌ ተቃዋሚ ፓርቲ የጦሩን እርምጃ ባይቃወምም ባስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንዲመሠረት ጠይቋል። ደቡብ አፍሪቃ መከላከያ ሚንስትሯን ወደ ሐራሬ ልካለች። SADEC በሚል የእንግሊዝኛ ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ አባል መንግስታት በጉዳዩ ላይ ተነጋግረዋል ።የአዉሮጳ ሕብረት በበኩሉ የዜምባቡዌ ሕገ-መንግሥት እንዲከበር አሳስቧል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic