የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ሥልጣን ለቀቁ | አፍሪቃ | DW | 21.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ሥልጣን ለቀቁ

ከአርባ ዓመት በላይ የመሩት የዛኑ-ፒ ኤፍ ፓርቲ ባለፈዉ ዕሁድ ከፓርቲዉ የመሪነት ሥልጣን ሽሯቸዋል።ዛሬ ደግሞ የዛኑ-ፒአፍ አባላት የሚበዙበት የሕገሪቱ ምክር ቤት ሙጋቤን ከሥልጣን የሚያስወግድበትን የክስ ሒደት ጀምሮ ነበር

Simbabwe Mugabe bei TV-Ansprache

የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ሥልጣን ለቀቁ

የዚምባብዌ የ37 ዘመን ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ።ሙጋቤ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ያስታወቁት ዛሬ ከቀትር በኋላ ለሐገሪቱ ምክር ቤት በፃፉት ደብዳቤ ነዉ።ምክር ቤቱ የሙጋቤ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ የደረሰዉ ሙጋቤን ከሥልጣን የሚወገዱበትን የሕግ ሒደት ከጀመረ በኋላ ነዉ።ሙጋቤን የሐገራቸዉ የጦር ጄኔራሎች ባለፈዉ ሳምንት ሮብ በቁም ካሰሯቸዉ ወዲሕ ሥልጣን እንዲለቁ ከራሳቸዉ ፓርቲ የሚደረግባቸዉ ግፊት ተጠናክሮ ነበር።ከአርባ ዓመት በላይ የመሩት የዛኑ-ፒ ኤፍ ፓርቲ ባለፈዉ ዕሁድ ከፓርቲዉ የመሪነት ሥልጣን ሽሯቸዋል።ዛሬ ደግሞ የዛኑ-ፒአፍ አባላት የሚበዙበት የሕገሪቱ ምክር ቤት ሙጋቤን ከሥልጣን የሚያስወግድበትን የክስ ሒደት ጀምሮ ነበር።የሙጋቤ ሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ሲነበብ ምክር ቤቱ በጭፈራ እና ጭብጨባ ተደበላልቋል።የደቡብ አፍሪቃ እና የአንጎላ መሪዎች  ሙጋቤን ለማነጋገር ዛሬ ሐራሬ ይገባሉ ተብሎም ነበር።ሙጋቤ ከስልጣን ካባረሯቸዉ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪቃ የተሰደዱት የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የፕሬዝደትነቱን ሥልጣን ለመያዝ ወደ ሐራሬ ይመለሳሉ ተብለዉ እየተጠበቁ ነዉ።የዚምባብዌ የሲቢል ማሕበረሰብ ጥምረት በበኩሉ ሁሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሳትፍ ፖለቲካዊ ዉይይት እንዲደረግ ጠይቋል።

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋዓለም ወልደየስ