የዚምባቡዌ ተስፋ | አፍሪቃ | DW | 17.09.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የዚምባቡዌ ተስፋ

ሐራሬ-ዚምባቡዌ።ሥምምነቱ ተፈረመ።።ፀደቀ-ተደነቀም።

default

ከግራ ወደ ቀኝ፥-ሙታምበራ፥ ሙጋቤና ችቫንገራይ

ሥምምነቱ ለዚምባቡዌ ሕዝብ የችግር-ስደት ኑሮዉ ፍፃሜ-መዳረሻ፣ የሰላም፣ ደሕንነቱ ተስፋ ጭላንጭል ለመሆኑ ባለፈዉ ሐሙስ ከሐራሬ እስከ ጁሐንስ በርግ የዉድቅት ፀጥታታን በፌስታ-ፍንደቃ ገፎ ከማደሩ የቀረበ ማረጋጋጪያ የለም።ለታቦ ኢምቤኪ ክብር-ለአፍሪቃዉን መሪዎች በሙሉ ደግሞ የአፍሪቃን ችግር መፍታት የመቻላቸዉ አኩሪ-ምሥክር፣ ለአፍሪቃ ሕዝብ ተስፋ ነዉ።በፖለቲካዉ ቀዉስ የታየዉ ሐቅ የቀዉሱ ምንጭ-ዚምባቡዌ ብቻ፥ አራጋቢ-አቀጣጣዮቹ፥ ፖለቲከኞቿ ብቻ፣አለመሆናቸዉን ማረጋገጡ ግን ርካታ፣ ደስታ፣ ክብር ኩራት ተስፋዉን እንዳያናጋዉ ያሰጋል።