የዙማ የፍርድ ቤት ውሎ | አፍሪቃ | DW | 06.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የዙማ የፍርድ ቤት ውሎ

የክሱ ጭብጥ ያኔ ደቡብ አፍሪቃ ከአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር በፈፀመችው የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የመሣሪያ ግዥ እንዲፈፀም አድርገዋል ፣ ከ24o ሺህ ፓውንድ በላይ ተከፍሏቸዋል የሚል ነበር ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:16

የዙማ የፍርድ ቤት ውሎ

የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጄኮቦ ዙማ በቀረበባቸው ክስ ዛሬ ደርባን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል። በፓርቲያቸው ግፊት ባለፈው የካቲት ወር ከሥልጣን የወረዱት ዙማ አሁን የቀረበባቸው ክስ በጎርጎሮሳዊው 1990ዎቹ ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ ከጦር መሣሪያ ግዥ ጋር በተያያዘ ፈጽመውታል የተባለ የሙስና ወንጀል ነው። የክሱ ጭብጥ ያኔ ደቡብ አፍሪቃ ከአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር በፈፀመችው የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የመሣሪያ ግዥ እንዲፈፀም አድርገዋል ፣ ከ24o ሺህ ፓውንድ በላይ ተከፍሏቸዋል የሚል ነበር ። ከዚህ ቀደም የቀረበው ይህ ክስ በጎርጎሮሳዊው 2009 ዓም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ውድቅ ተደርጎ ነበር። በቅርቡ አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ክሱ መቋረጡ ትክክል አይደለም ሲል በመወሰኑ ነው ክሱ እንደገና እንዲንቀሳቀስ የተደረገው። 

ገበያው ንጉሤ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic